የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽህፈት ቤት በ2016ዓ.ም  በክፍለ ከተማው በተሰሩ የጥናትና ምርምር ስራዎች ዙሪያ ጽብረቃ አካሄደ።

 (ግንቦት 13 /2016 ዓ.ም) በመርሀግብሩ ርዕሳነ መምህራን እና ሱፐርቫይዘሮችን ጨምሮ የወረዳ ትምህርት ጽህፈት ቤት ኃላፊዎችና ቡድን መሪዎች እንዲሁም የመምህራን ማህበር እና የተማሪ ወላጅ ማህበር አመራሮች ተሳታፊ ሆነዋል።

የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ከበደ ድሪባ በመርሀ ግብሩ መክፈቻ ባስተላለፉት መልዕክት በትምህርት ሴክተሩ የሚሰሩ ጥናትና ምርምሮች ለመማር ማስተማር ስራው የሚያበረክቱት አስተዋጽኦ ከፍተኛ ከመሆኑ ባሻገር እርስ በእርስ ልምድ መለዋወጥ የሚያስችሉ በመሆናቸው ጽብረቃው መዘጋጀቱን ገልጸው ዛሬ ከቀረቡት የጥናትና ምርምር ስራዎች መካከል የተሻለ ለሆኑት ዕውቅና እንደሚሰጣቸውና ምርምሮቹን ተግባራዊ ለማድረግ ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በጋራ እንደሚሰራም አስገንዝበዋል።

በውይይቱ በክፍለ ከተማና ወረዳ ትምህርት ጽህፈት ቤት ባለሙያዎች የተዘጋጁ 2 የጥናትና ምርምር ስራዎችን ጨምሮ በመምህራን የተሰሩ 3 ጥናትና ምርምሮች መቅረባቸውን የክፍለ ከተማው የመምህራን እና የትምህርት አመራር ቡድን መሪ አቶ ተሾመ ዘውዴ ጠቁመው የቀረቡት ጥናትና ምርምሮች በገላን የወንዶች አዳሪ ትምህርት ቤት እና በክፍለ ከተማው ሱፐርቫይዘሮች ተዳኝተው የተሻለ ለሆኑት እውቅና መሰጠቱን አስታውቀዋል።

በመርሀ ግብሩ ማጠቃለያ ከርዕስ መረጣ ጀምሮ ወቅታዊነትን፣ ችግር ፈቺነትን እንዲሁም የተቀመጡ የመፍትሄ ሀ ሳቦች ተግባራዊ መሆን የሚችሉ ስለመሆናቸው በዳኞች በተሰጠ ነጥብ የተሻሉ ለሆኑ የጥናትና ምርምር ስራዎች ዕውቅና ተሰቷል።

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

What Sapp: – https://whatsapp.com/channel/0029VaHFiBpA2pLF0lLslK2D

flickr :- https://www.flickr.com/photos/197652854@N04/

You Tube: https://www.youtube.com/@addisababaeducationbureau9728

TikTok፡- https://www.tiktok.com/@aaeducationbureau

Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc

Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/

Website: – aaceb.gov.et

Email;- aacaebc@gmail.com    

Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/

Leave a comment