9ኛው ከተማ አቀፍ የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ስፖርታዊ ውድድር በዛሬው እለት ተጀመረ።

(ግንቦት 10/2016 ዓ.ም) ስፖርታዊ ውድድሩ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮና ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ በጋራ “የትምህርት ቤቶች ስፖርታዊ ውድድር ለሰላም አብሮነትና ለሁለንተናዊ ብልጽግና” በሚል መሪ ቃል የሚካሄድ ሲሆን የመክፈቻ መርሀ ግብሩ  ተማሪዎች፣ መምህራን ፣ወላጆች ፣የትምህርት አመራሮችና ባለሙያዎችን ጨምሮ ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው አካላት በተገኙበት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሜዳ በድምቀት ተካሂዷል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ በስፖርታዊ ውድድሩ የመክፈቻ መርሀግብር ባስተላለፉት መልዕክት በትምህርት ቤቶች መካከል የሚካሄድ ስፖርታዊ ውድድር የተማሪዎችን የታመቀ አቅም በማውጣት በሀገር አቀፍና አለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ የሚሆኑ ስፖርተኞችን ከማፍራቱ ባሻገር በአካልና አዕምሮ ዳብረው በትምህርታቸው ውጤታማ የሆኑ ዜጎችን ለመፍጠር በሚደረገው እንቅስቃሴ የሚያበረክተው አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑን ጠቁመው የ9ኛው ስፖርታዊ ውድድር የመክፈቻ ፕሮግራም በድምቀት እንዲካሄድ አስተዋጽኦ ላደረጉ አካላት ምስጋና አቅርበዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ በላይ ደጀን በበኩላቸው ስፖርታዊ ውድድሩ ከዛሬ ጀምሮ ለ15 ቀናት አትሌቲክስና እግር ኳስን ጨምሮ በ6 የስፖርት አይነቶች እንደሚካሄድ ገልጸው ውድድሩ በፍጹም የስፖርታዊ ጨዋነት ተጀምሮ እንዲጠናቀቅ ጉዳዩ የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት በሙሉ ኃላፊነታቸውን በአግባቡ መወጣት እንደሚገባቸው አስገንዝበዋል።

በዛሬው የመክፈቻ ፕሮግራም በሴቶች 1500 ሜትር ውድድር እንዲሁም  ለሚኩራ ክፍለ ከተማ በሚገኘው የካ አባዶ እና ጉለሌ ክፍለ ከተማ በሚገኘው እንጦጦ አምባ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች መካከል የእግር ኳስ ውድድር ተካሂዷል።

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

What Sapp: – https://whatsapp.com/channel/0029VaHFiBpA2pLF0lLslK2D

flickr :- https://www.flickr.com/photos/197652854@N04/

You Tube: https://www.youtube.com/@addisababaeducationbureau9728

TikTok፡- https://www.tiktok.com/@aaeducationbureau

Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc

Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/

Website: – aaceb.gov.et

Email;- aacaebc@gmail.com    

Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/

Leave a comment