በቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ድጋፍና ክትትል ለሚያደርጉ ባለሙያዎች ኦረንቴሽን ተሰጠ።

(ግንቦት 9 ቀን 2016 ዓ.ም) ኦረንቴሽኑ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የዘርፈ ብዙና ቀዳማይ ልጅነት ትግበራ ዳይሬክቶሬት አማካይነት ድጋፍና ክትትሉን ለሚያደርጉ ባለሙያዎች የተሰጠ ሲሆን በመርሀ ግብሩ በተቋማቱ ለሚደረገው ድጋፍና ክትትል በተዘጋጀ ቼክ ሊስት ዙሪያ ገለጻ ተደርጓል።

 በቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶቹ የሚደረገው ድጋፍና ክትትል በተቋማቱ የሚስተዋሉ ክፍተቶችን በመለየትና የአቅም ግንባታ ስራዎችን በመስራት በቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ተቀራራቢ አፈጻጸም እንዲኖር ለማስቻል እንደሚያግዝ በከንቲባ ጽህፈት ቤት የቀዳማይ ልጅነት ፕሮግራም አስተባባሪ ዶክተር ታቦር ገብረ መድህን ገልጸዋል።

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የዘርፈ ብዙና ቀዳማይ ልጅነት ትግበራ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወይዘሮ በላይነሽ የሻው በበኩላቸው ኦረንቴሽኑ ባለሙያዎቹ  ድጋፍና ክትትል እንዲያደርጉ በተዘጋጀው ቼክ ሊስት ዙሪያ የጋራ ግንዛቤ ይዘው ወደ ተቋማቱ እንዲሄዱ ታስቦ መሰጠቱን ጠቁመው ድጋፍና ክትትሉ ከሰኞ ግንቦት 12/2016ዓ.ም ጀምሮ በቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች እንደሚካሄድም አስታውቀዋል።

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

What Sapp: – https://whatsapp.com/channel/0029VaHFiBpA2pLF0lLslK2D

flickr :- https://www.flickr.com/photos/197652854@N04/

You Tube: https://www.youtube.com/@addisababaeducationbureau9728

TikTok፡- https://www.tiktok.com/@aaeducationbureau

Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc

Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/

Website: – aaceb.gov.et

Email;- aacaebc@gmail.com    

Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/

Leave a comment