የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የሴቶችና ማህበራዊ ልማት ጉዳዬች ቋሚ ኮሚቴ አባላት ከክፍለ ከተማ ምክር ቤት የዘርፉ ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢዎች ጋር በጋራ በመሆን የትምህርት ቢሮን የዘጠኝ ወራት አፈጻጸም ገመገሙ።

(ግንቦት 8 ቀን 2016 ዓ.ም) ግምገማው በዋናነት የከተማውና የክፍለከተማ ምክር ቤት የሴቶችና ማህበራዊ ልማት ጉዳዬች ቋሚ ኮሚቴ  በትምህርት ተቋማት ባደረጉት የመስክ ምልከታ የተነሱ ሀሳቦችን ጨምሮ ቢሮው በ9 ወራት ከእቅድ አንጻር ያከናወናቸው ተግባራት አፈጻጸምን በመገምገም በቀጣይ ከቋሚ ኮሚቴ አባላቱ የሚሰጡ ግብረ መልሶችን  መሰረት በማድረግ ውጤታማ ስራ መስራት እንዲችል ታስቦ መካሄዱን ተገልጿል።

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የሴቶችና ማህበራዊ ልማት ጉዳዬች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወይዘሮ ዘይነባ ሽኩር በሮው የተማሪዎችን ውጤት ለማሻሻል  እየተከናወኑ የሚገኙ ተግባራት ምን ደረጃ ላይ እንደሚገኙ ከማየት ባሻገር በእቅድ ተይዘው  በትግበራ ወቅት የተስተዋሉ ማነቆዎችን ለመቅረፍ ታስቦ ሱፐርቪዥኑ መካሄዱን ገልጸው የቋሚ ኮሚቴ አባላቱ በትምህርት ቤቶች ባደረጉት ምልከታ አበረታች ውጤቶችን ማየታቸውን በመጥቀስ  በቀጣይ የተሻለ ስራ መስራት እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ የትምህርት ስራ የሁሉንም ባለድርሻ አካላት  ተሳትፎ የሚፈልግ ተግባር እንደመሆኑ ቢሮው ከተለያዩ አካላት ጋር በቅንጅት በመስራት ላይ እንደሚገኝ ጠቁመው የቢሮው ማኔጅመንት አባላት በየዕለቱ ስራዎችን በመገምገም አቅጣጫ እያስቀመጠ በመሄድ ላይ እንደሚገኝ በመጥቀስ የቋሚ ኮሚቴ አባላቱ ለትምህርት ሴክተሩ ለሚያደርጉት ድጋፍና ክትትል ምስጋና አቅርበዋል።

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

What Sapp: – https://whatsapp.com/channel/0029VaHFiBpA2pLF0lLslK2D

flickr :- https://www.flickr.com/photos/197652854@N04/

You Tube: https://www.youtube.com/@addisababaeducationbureau9728

TikTok፡- https://www.tiktok.com/@aaeducationbureau

Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc

Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/

Website: – aaceb.gov.et

Email;- aacaebc@gmail.com    

Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/

Leave a comment