ቀን 5/7/2015 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት 2ኛ ዓመት የስራ ዘመን 3ኛ መደበኛ ጉባኤውን ማካሄድ ጀምራል፡፡

ምክርቤቱ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ2015 ዓም የመጀመሪያ 6 ወራት እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት  ላይ ይወያያል፣ ረቂቅ  ማሻሻያ አዋጅ ላይ  ተወያይቶ ማጽደቅና  ሌሎች አጀንዳዎች ላይ እንደሚወያይ ይጠበቃል።

ከንቲባ አዳነች አቤቤ  የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ2015 ዓም የመጀመሪያ 6 ወራት እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት  ያቀረቡ ሲሆን በሪፖርታቸዉ ፡- “የፀረ-ሌብነት ትግልን በማጠናከር፡ የህግ በላይነት የማስከበር፣ የተጠያቂነት ለማስፈን በሕዝባዊ ንቅናቄ የተደገፉ ስራ እየተሰራ ነው፡፡ የፀረ-ሙስና እና ስነ- ምግባር ኮሚሽን በአዲስ መልክ ተደራጅቶ ስራ ጀምሮአል:: በከተማ ደረጃ የፀረ ሙስና ንቅናቄ ግብረ ሃይል ተቋቁሞ ከህብረተሰቡ ጥቆማ በመቀበል  215 አመራሮች፣ ባለሙያዎችና ደላሎች በህግ ቁጥጥር ስር ሆነው ጉዳያቸው በፍትህ ሂደት ላይ ይገኛል፡፡

ይሄም በዝርዝር ሲታይ የካ ክ/ከተማ 40፤ ንፋስ ስልክ ላፍቶ 42፤  ለሚ ኩራ 48፤ ልደታ 26፤ አቃቂ ቃሊቲ 33፤ በማዕከልና ሴክተሮች 26 የሚሆኑ በህግ ተጠያቂ ሆነዋል፡፡

በተጨማሪም ከማዕከል አስከ ወረዳ ባሉ ተቋማት 3,584 አመራርና ሰራተኞች በተለያዩ የዲሲፕሊን ግድፈቶች አስተዳደራዊ እርምጃ እንዲወሰድባቸው ተደርጓል ያሉ ሲሆን፡፡

ባለፉት 6 ወራት የህብረተሰቡን የኑሮ ጫና ለማቅለል የተከናወኑ ዋና ዋና ስራዎችን በተመለከተ :-

•  የምርት አቅርቦትን በማሳደግ የዋጋ ግሽበትና የኑሮ ዉድነትን ለማረጋጋት በተሰራው ስራ፤ 170,128 የሰብል ምርት በገበያ ማዕከላት ትስስር መፍጠር ተችሏል፡፡

•  የእሁድ ገበያ(Sunday Market) በሁሉም ክ/ከተሞች በ137 የገበያ መዳረሻዎች በማስፋፋት የግብርና ምርቶች ከአርሶ አደሩ ወደ ተጠቃሚው በቀጥታ እንዲደርሱ በማድረግ ሸማቹ በተመጣጣኝ ዋጋ ምርቶችን እንዲያገኝ እየተደረገ ይገኛል

•  የመሠረታዊ ፍጆታ ሸቀጦች አቅርቦት ለህብረትሰቡ በፍትሃዊነት ተደራሽ ከማድረግ አንፃር 272,777 ስኳር ማሰራጨት ተችሏል።

•  10.9  ሚሊዮን ሊትር ፓልም ዘይት ማሰራጨት ተችሏል

•  194 ሚሊዮን የሸገር ዳቦ በሸገር ዳቦ በመሽጫ ሱቆች ማሰራጨት ተችሏል

•  ከሸገር የዳቦ ፋብሪካ በተጨማሪ የተገነቡት የዳቦ ፋብሪካዎች ቁጥር 25 ማድረስ ተችሏል

•  የከተማ አስተዳደሩ በመደበው 1.4 ቢሊዮን የተዘዋዋሪ ብድር በመጠቀም በድምሩ 356,761 ኩንታል ጤፍ በሸማች ኅብረት ሥራ ማህበራት በኩል በማቅረብ ገበያ የማረጋጋት ስራ ተሰርቷል

•  ለትምህርት ቤት ምገባ የወቅቱን ኑሮ ውድነት መነሻ በማድረግ በዓመት ተጨማሪ 54ዐ ሚሊዮን ብር ተመድቦ የመጋቢ እናቶችን ጫና የመቀነስ እና የተማሪዎችን ምገባ የተሻለ ለማድረግ የሚያስችል ስራ ተሰርቷል

•  በዘላቂነት የኑሮ ውድነት ጫና  ለመቀነስና ገበያን ለማረጋጋት በአዲስ አበባ የመግቢያ በሮች ማለትም በኮልፌ ፣ በንፋስልክ ላፍቶ ፣ በለሚ ኩራ እና በአቃቂ ክፍለ ከተሞች አራት ትላልቅ ሁለገብ የግብርና ምርቶች ማከፋፈያ ማዕከላት ግንባታ በዚህ በጀት ዓመት ለማጠናቀቅ 24 ሰዓታት እየተሰራ ይገኛል

. የሌማት ትሩፋት ስራችን አዲስ የልማት ከፍታ ጉዞ በሚል ከጥቅምት 27 ጀምሮ 52,228 ለሚሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች ስልጠና በመስጠት ወደ ተግባር እንዲገቡ ተደርጓል፡፡ በተለይ የወተት፣ የዶሮ ስጋ ፣ እንቁላል እና የማር ምርታማነት በማሳደግ እንዲሁም የጓሮ አትክልት በማምረት ያለንን አቅም እና ጸጋ ወደ ተግባር በመቀየር የከተማችንን ነዋሪዎች የኑሮ ጫና ለማቅለል እየተሰራ ይገኛል

. በከተማችን በቀን አንድ ግዜ መመገብ ለማይችሉ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ላሉ ነዋሪዎች በ15 የምገባ ማዕከላት 30ሺህ ለሚሆኑ ነዋሪዎች የምገባ ፕሮግራም ተጠቃሚ ማድረግ ተችላል ብለዋል::

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ

Ticktack፡- tiktok.com/@aaeducationbureau

Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc

Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/

Website: – aaceb.gov.et

Email;- aacaebc@gmail.com

Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s