ቀን 1/7/2015 ዓ.ም

ወደ ቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ተቋማት ለሚገቡ አዲስ ስልጣኞች የተማሪ ቅበላ ማስጀመሪያ መርሃ-ግብር ተካሄደ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት እና የቴክኒክና ሙያ ስልጠና እና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮዎች በ2015 የትምህርት ዘመን ወደ ቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ተቋማት ለሚገቡ አዲስ ስልጣኞች የተማሪ ቅበላ ማስጀመሪያ  መርሃ-ግብር በጋራ አካሄደዋል፡፡

የተማሪ ቅበላ ማስጀመሪያ መርሃ-ግብሩ በእንጦጦ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ቅጥር ግቢ ውስጥ የተካሄደ ሲሆን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ ፣ የቢሮ ምትል ቢሮ ሀላፊ አቶ አድማሱ ደቻሳ ፣ የቴክኒክና ሙያ ስልጠና እና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ሀላፊ ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅ ፣ የክፍለ ከተማ ትምህርት ጽፈት ቤት ሀላፊዎች ፣ የየማስልጠኛ ኮሌጁ ሀላፊዎች ፣ የአሰልጣኞች ሙያ ማህበራት ፣ አስልጣኝ መምህራን፣ ተማሪዎች እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ የቴክኒክና ሙያ ስልጠና በተጨባጭ ተግባር የታገዘ  በቴክኒክ ትምህርት መስልጠን ለሚፈልጉ እንዲሁም በተለያዩ የሙያ ዘርፎች አዳዲስ ክህሎቶችን ማዳበር ለሚፈልጉ ስዎች የሚሰጥ የፈጠራ ክህሎትን ለማስተማር የሚያስችል ተመራጭ የትምህርት ዘርፍ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ አክለውም ተማሪዎች በሚፈልጉት የሙያ ዘርፍ እና ደረጃ ላይ መማር የሚችሉ መሆኑን አመላከተዋል፡፡

የቴክኒክና ሙያ ስልጠና እና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ሀላፊ ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅ በበኩላቸው ዘንድሮ ወደ ቴክኒክና ሙያ ተቋማት ለሚገቡ ተማሪዎች የቴክኒክና ሙያ ማስልጠኛ ተቋማት ሙሉ ዝግጅት ማድረጋቸውን ገልጸዋል፡፡በተጨማሪም 108 የሙያ አይነቶች በ8 ኮሌጆች ስልጠናዎች የሚሰጡ መሆኑን አሳውቀወል፡፡

የአዲስ አበባ የቴክኒክና ሙያ አስልጣኞች ማህበርን በመወከል መልዕክት ያስተላለፉት አቶ ትጉ መሀሪ ማህበሩ የመደገፍና የማስተማር ድርሻውን ይወጣል ብለዋል፡፡

በመርሃ-ግበሩ የማስልጠኛ ኮሌጆችም ስራዎች በተሳታፊዎች ተጎብኝተዋል፡፡

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

 Blog: – https://aacaebc.blogspot.com

You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ

TikTok፡- tiktok.com/@aaeducationbureau

Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc

Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s