ቀን 30/6/2015 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የአዲሱን ስርዓተ ትምህርት አተገባበር በተመለከት ከርዕሳነ መምህራን ጋር ውይይት አካሄደ።

በውይይቱ የክፍለ ከተማ ትምህርት ጽህፈት ቤት ኃላፊዎችና የስርአተ ትምህርት ትግበራ ቡድን መሪዎችን ጨምሮ ስርአተ ትምህርቱ መሉ ለሙሉ ተግባራዊ የተደረገባቸው አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሳነ መምህራን እና በሙከራ ደረጃ ተግባራዊ የተደረገባቸው ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሳነ መምህራን ተሳታፊ ሆነዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ አድማሱ ደቻሳ የውይይቱን አላማ አስመልክቶ ባስተላለፉት መልዕክት አዲሱን ስርአተ ትምህርት መሰረት በማድረግ ተዘጋጅተው በየትምህርት ቤቱ ለመማር ማስተማር አገልግሎት የዋሉ የተማሪዎች የመማሪያ መጽሀፍትም ሆኑ የመምህር መምሪያ ይዘትን በመገምገም በቀጣይ ወደህትመት ሲገባ ተገቢውን ማስተካከያ ማድረግ እንዲቻል ታስቦ ውይይቱ መካሄዱን ጠቁመው የውይይቱ ተሳታፊ ርዕሳነ መምህራንም ከነገ ጀምሮ  በየዲፓርትመንቱ ለመምህራን ኦረንቴሽን በመስጠት ይዘቱን አስገምግመው ሪፖርት መላክ እንደሚጠበቅባቸው አስረድተዋል።

አዲሱን ስርአተ ትምህርት በአግባቡ ተግባራዊ ለማድረግ የመምህራንም ሆነ የትምህርት አመራሮች ሚና ከፍተ ኛ በመሆኑ የመጽሀፍቶቹን ይዘት በአግባቡ መግምገምና ተገቢውን ግብረ መልስ መስጠት እንደሚገባ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊው አቶ አሊ ከማል ገልጸው በዋናነት በግምገማቸው የስርአተ ትምህርቱን ይዘት ግልጽነት እና ተገቢነት ጨምሮ ሌሎች የመገምገሚያ መስፈርቶችን መሰረት በማድረግ ግምገማውን ማካሄድ እንደሚገባቸው አስገንዝበዋል።

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

 Blog: – https://aacaebc.blogspot.com

You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ

TikTok፡- tiktok.com/@aaeducationbureau

Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc

Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s