ቀን 29/6/2015 ዓ.ም

አለም አቀፍ የሴቶች ቀን በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ከትምህርት ማህበረሰቡ ጋር በድምቀት ተከበረ፡፡

በአለም አቀፍ ደረጃ ለ112ኛ ጊዜ በኢትዮጵያ ደረጃ ደግሞ ለ47 ጊዜ ‹‹ እኔ የእህቴ ጠባቂ ነኝ›› በሚል መሪ ቃል የ2015 ዓ.ም የሴቶች ቀንን በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት አዘጋጅነት ሴት ርዕሰ መምህራን፣ ሴት ሱፐርቫይዘሮች፣ ሴት ዲፓርትመንት ተጠሪዎች፣ የስርዓተ ጾታ ክበብ ተጠሪ መምህራንና አባል ተማሪዎች፣ መጋቢ እናቶች፣ ሴት ቡድን መሪዎች፣ ሴት የትምህርት ባለሙያዎች እና የክፍለ ከተማው ሴት መምህራን ማህበር በተገኙበት በድምቀት የተከበረ ሲሆን በእለቱም ሴት ርዕሰ መምህርት እና ሴት ሱፐርቫይዘር የህይወት ተሞክሮአቸውን ለታዳሚዎች በማካፈል ተማሪዎች የተለያዩ ስነ-ጽሁፎችና ውዝዋዜዎችን በማቅረብ በደማቅ ሁኔታ ተከብሯል፡፡

ጠንካራ ሰራተኛ እና ጠንካራ መሪ ለመሆን ጠንክሮ መስራትና በየደረጃው ያለውን ኃላፊነት በመቀበል አርአያ ሆኖ መገኘትና ሴት ተማሪዎቻችንን ቀርበን ድጋፍ በመስጠት ውጤታማ ተማሪዎች እንዲሆኑ ማድረግ እንደሚገባ የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊ ሳምራዊት ቅባቱ ገልጸዋል፡፡ በመጨረሻም ለተማሪ ነጂባ አማን ሽልማት በመሰጠት ፕሮግራሙ ተጠናቋል፡፡

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

 Blog: – https://aacaebc.blogspot.com

You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ

TikTok፡- tiktok.com/@aaeducationbureau

Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc

Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s