ቀን 28/6/2015 ዓ.ም

በአዲስ አበባ ከተማ የተማሪዎች ውጤትን ለማሻሻል የሚያስችል የዋንጫ ርክክብ ተካሄደ።

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በከተማ አስተዳደሩ ከተማ አቀፍ እና ሀገራቀፍ ፈተና ተፈታኝ የሆ ኑ የ6ኛ ፣የ8ኛ እና የ12ኛ ክፍል ተማሪዎችን ውጤት የላቀ እንዲሆን እና ተማሪዎች በፍክክር መንፈስ የተሻለ ውጤት መስመዝገብ እንዲችሉ የተማሪዎች ውጤት ማሻሻያ የዋንጫ ርክክብ ማስጀመሪያ መርሃ ግብር አካሄዳል፡፡

ዋንጫው ከአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ለአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ትምህርት ፅ/ቤት ርክክብ የተደረገ ሲሆን በቀጣይ በሁሉም ክፍለከተሞችና በሁሉም ትምህርት ቤቶች  የሚዘዋወር ይሆናል።

ዋንጫው በ6ኛ ፣ 8ኛ እና 12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍና ከተማ አቀፍ ፈተናዎች ላይ የሚኖረውን ውጤት ለማሻሻል እንዲቻል በተማሪዎች ላይ መነቃቃትንና የውድድር መንፈስን ለማሳደግ  ትኩረት ተሰጦ የሚሰራበት ነው።

መድረኩ በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ አዘጋጅነት በፊታውራሪ ሀብተጊዮርጊስ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት የተጀመረ ሲሆን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ሀላፊ አቶ አሊ ከማል ፣ የቢሮ ሀላፊ አማካሪ ወ/ሮ አበበች ነጋሽ ፣ የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽፈት ቤት ሀላፊ ሳምራዊት ቅባቱ ፣ ርዕሳነ መምህራን ፣ ባለሙያዎች ፣ ወላጆች ፣ መምህራን እና ተማሪዎች ተሳታፊ ሁነዋል፡፡

በመድረኩ በ2015 የትምህርት ዘመን ከተማ አቀፍ እና ሀገራቀፍ ፈተና ተፈታኝ የሆኑ የ6ኛ ፣ የ8ኛ እና የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች በፍክክር መንፈስ የላቀ ውጤት ማስመዝገብ እንዲችሉ በሶስቱም የክፍል ደረጃዎች ላይ ተማሪዎች ተግተው እንዲሰሩ እንደሚያደርግ የተመላከተ ሲሆን በዓመቱ መጨረሺያ ላይ ዋንጫዎቹ ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች ላሉባቸው ክፍለ ከተማዎች የሚበረከቱ እንደሚሆኑ ተገልጻል፡፡

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

 Blog: – https://aacaebc.blogspot.com

You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ

TikTok፡- tiktok.com/@aaeducationbureau

Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc

Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s