የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የእቅድ በጀት ክትትልና ግምገማ ዳይሬክቶሬት የ2015 ዓ.ም የ6ወር የቢ ኤስ ሲ እቅድ አፈጻጸም ምዘና ለሚያካሂዱ መዛኞች ኦረንቴሽን ሰጠ፡፡
ምዘናው እስከ 2014 ዓ.ም ድረስ በለውጥና መልካም አስተዳደር ዳይሬክቶሬት አማካይነነት ሲካሄድ ቆይቶ ዘንድሮ የምዘና ስርዓቱ በእቅድ በጀት ክትትልና ግምገማ ዳይሬክቶሬት እንዲመራ በተወሰነው መሰረት ከትምህርት ቤት ጀምሮ እስከ ትምህርት ቢሮ ድረስ አስሩን ዋና ዋና ግቦች መነሻ በማድረግ አድርጎ የሚካሄድ ሲሆን በኦረንቴሽኑ ከ400 በላይ መዛኞችና አስተባባሪዎች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡
በትምህርት ተቋማት የሚካሄድ የቢ ኤስ ሲ እቅድ አፈጻጸም ምዘና ተቋማቱ ያሉበትን ደረጃ ለማወቅ ከማስቻሉ ባሻገር የውድድር መንፈስ በመፍጠር በቀጣይ የተሻለ ስራ መስራት እንደሚያስችል በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የእቅድ በጀት ክትትልና ግምገማ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተሩ አቶ ጌታሁን ለማ ገልጸው በምዘና ሂደቱ በመዛኝነት የሚሳተፉ የትምህርት ባለሙያዎችም ሆኑ አመራሮች ለምዘናው የተዘጋጁ የመመዘኛ መስፈርቶችን መሰረት በማድረግ ምዘናውን ማካሄድ እንደሚገባቸው አስገንዝበዋል፡፡
ምዘናው ከነገጀምሮ በሁሉም የመንግስት አንደኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች እንዲሁም የወረዳና ክፍለከተማ ትምህርት ጽህፈት ቤቶች ጨምሮ በአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ በሚገኙ የስራ ክፍሎች የሚካሄድ ሲሆን ተመዛኝ ተቋማትም መዛኞች ለምዘና በሚሄዱበት ወቅት ተገቢውን መረጃ በማቅረብ ለምዘና ስርአቱ ውጤታማነት የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ማበርከት እንደሚጠበቅባቸው ዳይሬክተሩ አስረድተዋል፡፡
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!
You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ…
TikTok፡- tiktok.com/@aaeducationbureau
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication
Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/
Website: – aaceb.gov.et
Email;- aacaebc@gmail.com
Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/