ቀን 10/6/2015 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ከአዲስ አበባ ከተማ ትራንስፖርት ቢሮ ጋር በጋራ በመሆን በተማሪዎች የትራንስፖርት አገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት አካሄደ።

ውይይቱ በዋናነት በግል ትምህርት ቤቶች አከባቢ የሚታዩ የትራፊክ መጨናነቆችን ለመቅረፍ በተዘጋጀ የመፍትሄ ኃሳብ ዙሪያ ከግል ትምህርት ቤት ባለሀብቶች ጋር የተካሄደ ሲሆን የግል ትምህርት ቤቶች እስከ 70 ተማሪ መያዝ የሚችሉ የተማሪ አውቶብሶችን እንዲጠቀሙና የከተማውን የትራንስፖርት አገልግሎት መጨናነቅ ማቃለል የሚያስችል የመወያያ ሀሳብ ቀርቦ ሰፊ ውይይት ተካሂዷል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ በውይይቱ ባስተላለፉት መልዕክት በግል ትምህርት ቤቶች አከባቢ በተለይም በተማሪዎች መግቢያና መውጫ ሰዓት ከፍተኛ የትራንስፖርት መጨናነቅ እንደሚስተዋል ገልጸው በነዚህ ትምህርት ቤቶች የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ የተማሪ አውቶብሶችን መጠቀም ቢቻል ችግሩን ከመቅረፉ ባሻገር ተማሪዎች በሰዓቱ ትምህርት ቤት ደርሰው ትምህርታቸውን በአግባቡ መከታተል እንዲችሉ የሚያስችል የመፍትሄ ሀሳብ በመሆኑ በቀጣይ ለተግባራዊነቱ ጉዳዩ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር  በጋራ እንደሚሰራ አስገንዝበዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ምትኩ አማረ በበኩላቸው ቢሮው ቀደም ሲል 94 የሚደርሱ መለስተኛ አውቶብሶችን ለግል ትምህርት ቤቶች አቅርቦ ተማሪዎች የትራንስፖርት አገልግሎት እንዲያገኙ ማስቻሉን ገልጸው አሁን የቀረበው አማራጭ ተማሪዎች ላይ የሚደርስ የትራፊክ አደጋን ከመቅረፉ ባሻገር የትራንስፖርት አገልግሎቱን ማዘመን የሚያስችል አሰራር በመሆኑ ቢሮው ከ2016 ዓ.ም ጀምሮ ፍላጎትን መሰረት በማድረግ የግል ትምህርት ቤቶችን ወደዚህ አገልግሎት የማስገባት ስራውን እንደሚጀምር አስታውቀዋል።

የውይይቱ ተሳታፊዎችም የቀረበው አማራጭ በትምህርት ቤቶቻቸው አከባቢ የሚስተዋሉ የትራፊክ ፍሰት ችግሮችን ከመቅረፉ ባሻገር የተማሪዎችን የእርስ በእርስ ግንኙነት የሚያጠናክር በመሆኑ ለተግባራዊነቱ የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነት ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸውምን አስረድተዋል።

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ

TikTok፡- tiktok.com/@aaeducationbureau

Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc

Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/

Website: – aaceb.gov.et

Email;- aacaebc@gmail.com

Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s