ቀን 7/6/2015 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የፈተና ዝግጅትና አስተዳደር ዳይሬክቶሬት የ6ኛ እና 8ኛ ክፍል ፈተናን ለማስተዳደር በተዘጋጀ አዲስ ሲስተም ዙሪያ ለግል ትምህርት ቤት ርዕሳነ መምህራን ኦረንቴሽን ሰጠ፡፡

ሲስተሙ ቀለም ሜዳ ቴክኖሎጂስ በተሰኘ ሀገር በቀል ድርጅት የበለጸገ ሲሆን አምና በኦሮሚያ ክልል ተግባራዊ ተደርጎ ውጤታማ መሆኑን የድርጅቱ መስራች እና የወሎ ዩኒቨርሲቲ የሶፍትዌር ምህንድስና መምህር የሆኑት አቶ ገብረመድህን መኮንን ገልጸው ሲስተሙ የ6ኛ እና 8ኛ ክፍል ሚኒስትሪ የሚወስዱ ተማሪዎችንም ሆነ ፈታኝ ትምህርት ቤቶችን አጠቃላይ መረጃ የሚያስተዳድር መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ  ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ዳኘው ገብሩ በመርሀ ግብሩ መክፈቻ ባስተላለፉት መልዕክት የ2015ዓ.ም የትምህርት ዘመን በከተማ አስተዳደሩ አዲሱን ስርአተ ትምህርት መሰረት በማድረግ የ6ኛ ክፍል ሚኒስትሪ የሚሰጥበት አመት መሆኑን ጠቁመው የ6ኛም ሆነ የ8ኛ ክፍል ፈተና በቴክኖሎጂ ታግዞ ተፈታኝ ተማሪዎችን ኦን ላይን ከመመዝገብ ጀምሮ አጠቃላይ የፈተና ስርአቱን በቀላሉ መቆጣጠር የሚያስችል ሲስተም ቀለም ሜዳ ቴክኖሎጂስ በተሰኘ ሀገር  በቀል ድርጅት ተዘጋጅቶ ወደስራ ለመግባት ቅድመ ዝግጅት መጠናቀቁን በመግለጽ ሲስተሙ በአግባቡ ተግባራዊ እንዲሆን በየደረጃው የሚገኙ ጉዳዩ የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነት በአግባቡ መወጣት እንደሚጠበቅባቸው አስገንዝበዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የፈተና ዝግጅትና አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ዲናኦል ጫላ በበኩላቸው ሲስተሙ ቀላል እና ምቹ ከመሆኑ ባሻገር በሀገር በቀል ድረጅት መዘጋጀቱ ከዚህ ቀደም ለውጪ ድርጅቶች ሲወጣ የነበረውን ከፍተኛ ገንዘብ ማስቀረቱን ገልጸው  በ2015ዓ.ም የ6ኛ እና 8ኛ ክፍል ፈተና የሚያስፈትኑ ትምህርት ቤቶች ሲስተሙን በመጠቀም ከየካቲት 13 እስከ 17/2015 የ6ኛ ክፍል ተፈታኞችን እንዲሁም ከየካቲት 20 እስከ 24/2015ዓ.ም ድረስ ደግሞ የ8ኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎችን ኦን ላይን እንዲመዘግቡ ፕሮግራም መውጣቱን  አስረድተዋል፡፡

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ

TikTok፡- tiktok.com/@aaeducationbureau

Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc

Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/

Website: – aaceb.gov.et

Email;- aacaebc@gmail.com

Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s