የጉለሌ ክፍለ ከተማ ትምህርት እና የትምህርት ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ጉለሌ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች በአዲሱ ሥርዓተ ትምህርት ትግበራ ላይ ከትምህርት ተቋማት ባለቤቶች ጋር ውይይት አካሄዱ።
ጽህፈት ቤቶቹ በአዲሱ ስርዓተ ትምህርት የብዝሃ ቋንቋ ስርዓት አተገባበር ዙሪያ ከግል የትምህርት ተቋማት ባለቤቶች ጋር የተወያዩ ሲሆን ከአፍ መፍቻ ቋንቋ በሁለተኛነት በሚሰጠው ተጨማሪ ቋንቋ የትምህርት አሰጣጥ ዙሪያ የጉለሌ ክፍ ለከተማ ትምህርት ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ሚሊዮን ኮራ ገለጻ አድርገዋል፡፡
ከ7ኛ ክፍል ጀምሮ በሁሉም ትምህርት ቤቶች የአገር ውስጥ ቋንቋ መማራቸው እንደተጠበቀ ሆኖ ሁሉንም የትምህርት ዓይነቶችን በእንግሊዚኛ መማር እንዲችሉ መደረጉንም ገልጸዋል፡፡
የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን ጉለሌ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ፍቅሩ ገቢሳ በአዲሱ የሥርዓተ ትምህርት ትግበራ የትምህርት ጥራትን ከየትኛውም ጊዜ በላይ ማረጋገጥ እንደሚቻል አመላክተዋል፡፡
በውይይት መድረኩ ላይ የግል ትምህርት ቤቶች ባለቤቶች እንዲሁም የሚመለከታቸው አካላት ተገኝተው ውይይት መካሄዱን ጉለሌ ኮሙኒኬሽን ዘግባል፡፡
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!
You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ…
TikTok፡- tiktok.com/@aaeducationbureau
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication
Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/
Website: – aaceb.gov.et
Email;- aacaebc@gmail.com
Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/