ከ4ሺህ በላይ የትምህርት ባድርሻ አካላትን ያሳተፈ ስልጠና በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ እየተካሄደ ነው።
የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ “በተደራጀ የባለድርሻ አካላት ተሳትፎ የትምህርት ጥራትን እናረጋግጣለን” በሚል መነሻ ፅሑፍ በትምህርት ጥራት ዙሪያ 4,734 የመንግስትና የግል ትምህርት ተቋማት መምህራን፣ርዕሰ መምህራን ፣የትምህርት ባለሙያዎች እንዲሁም አስተዳደር ሠራተኞች ተሳታፊ የሆኑበት ለሁለት ቀናት የሚቆይ ስልጠና እየሠጠ ይገኛል።
በዚህም ሀያ ሁለት የመንግስት ትምህርት ቤቶች ቡድኖችና በሀምሳ ሁለት የግል ትምህርት ቤቶች ቡድኖች በአጠቃላይ በሠባ አራት የቡድን ውይይቶች እየተካሄዱ እንደሚገኝም ተገልጿል።
በዚህ ስልጠና ላይ በትምህርት ጥራት ዙሪያ የባለድርሻ አካላት ሚና ምን መምሠል እንዳለበት የሚጠቁም ሰነድ የቀረበ ሲሆን በሰነዱም እንደ ሀገር በትምህርት ተደራሽነትና ጥራት የተሠሩ በርካታ ስራዎች ያሉ ጥንካሬዎችንና ድክመቶች ምን እንደሆኑ እና የከተማ አስተዳደሩ በመማር ማስተማር ሂደት ላይ ያሉ አንኳር ችግሮች ምን እንደሆ በሚጠቁሙ አጀንዳዎች ላይ ሰፊ ውይይቶችን እያካሄደ ነው።
ይህንን የውይይት መድረክ በንግግር የከፈቱት የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሲሳይ ኬኔ እንዳሉት ለሠላም ያለንን ፍላጎት በትምህርት ጥራት ላይ በመድገም የትምህርት ባለድርሻ አካሉ በትውልድ ግንባታ ላይ ለሚደረገው እርብርብ የበኩሉን ኃላፊነት ሊወጣ ይገባልም ማለታቸዉን ለየሚ ኩራ ኮሚኒኬሽን ዘግባል፡፡
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!
You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ…
TikTok፡- tiktok.com/@aaeducationbureau
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication
Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/
Website: – aaceb.gov.et
Email;- aacaebc@gmail.com
Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/