በዳግማይ ሚኒሊክ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት በማርሽ ባንድና በዘመናዊ ኦኬስትራ ሙዚቃ የሰለጠኑ ተማሪዎች ተመረቁ፡፡
በአራዳ ክፍለ ከተማ የሚገኘው የዳግማይ ሚኒሊክ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ከሚያዚያ 2014 ዓ.ም እስከ ጥር 30/2015 ዓ.ም በማርሽ ባንድና በዘመናዊ ኦኬስትራ ሙዚቃ ያሰለጠናቸውን 35 ተማሪዎች አስመረቀ፡፡
በምርቃት ስነ-ስርዓቱ ታላላቅ የኪነ-ጥበብ ባለሙያዎች፣ መምህራን፣ አመራሮች፣ የተመራቂ ቤተሰቦችና እንግዶች እንዲሁም የቀድሞ ተማሪዎች ተገኝተዋል፡፡
የዳግማይ ሚኒሊክ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ዋና ርዕሰ መምህር አቶ ኢብራሂም ሰዒድ በትምህርት ቤታችን ለረጅም አመታት ተቋርጦ የቆየውን የማርሽ ባንድ በበጎ ፈቃደኛ መምህራንና ተማሪዎች ዳግም ተጀምሮ ዛሬ ላይ ተማሪዎችን ለምርቃት በማብቃቱ ደስተኞች ነን ብለዋል፡፡
ብዙ የኪነ-ጥበብ ባለሙያዎች መነሻ ትምህርት ቤት እንደመሆኑ ትምህርት ቤቶች ላይ ከፍተኛ ትኩረት ሰጥቶ መስራት ያስፈልጋል ያሉት ክቡር ዶ/ር አርቲስት ዳዊት ይፍሩ በየትምህርት ቤቱ ለተማሪዎች ከልጅነታቸው ጀምሮ የሚሰጠውን የሙዚቃ ትምህርት ማጠናከር ለኢትዮጵያ የጥበብ እድገት ወሳኝ ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡
አቶ ዳዊት አክለውም የተማራችሁትን በየጊዜው እየተለማመዳችሁ በሙዚቃው ዘርፍ አሻራችሁን ማኖር ይጠበቅባችኋል ሲሉ ለተመራዊ ተማሪዎች መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
በመጨረሻም ተመራቂ ተማሪዎች የተለያዩ ጣዕመ ዜማዎችን አቅርበዋል፡፡
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!
You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ…
TikTok፡- tiktok.com/@aaeducationbureau
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication
Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/
Website: – aaceb.gov.et
Email;- aacaebc@gmail.com
Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/