ሲ ኤም ኤ ሲ ጂ ኤም (CMA CGM) የተሰኘ ገብረሰናይ ድርጅት ግምታቸው አስር ሺ የአሜሪካ ዶላር የሚያወጡ የምግብ ማብሰያ ብረት ድስቶችን (ጎላዎች) ለትምህርት ቤቶች አበረከተ፡፡
የማብሰያ ብረት ድስቶቹ መጠናቸው ከፍተኛ ከመሆኑ ባሻገር ብዘታቸው 42 ሲሆን በዋናነትም በየትምህርትቤቶቹ ያለውን የተማሪዎች የምገባ አገልግሎት እንዲያግዙ በማሰብ ድጋፍ መደረጉን በዛሬው እለት ከመጋቢ እናቶች ጋር ርክክብ በተደረገበት ወቅት ተገልጻል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ ድጋፉን ከግብረሰናይ ድርጅቱ ተወካዮች በተረከቡበት ወቅት ባስተላለፉት መልዕክት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርት ቤቶች የምገባ አገልግሎት ከተጀመረ ጊዜ አንስቶ ተማሪዎች ሙሉ ትኩረታቸው በትምህርታቸው ላይ እንዲሆን ከማስቻሉ ባሻገር ለወላጆች እፎይታ መስጠቱን እና ለበርካታ መጋቢ እናቶች ደግሞ የስራ እድል መፍጠሩን ጠቁመው ሲ ኤም ኤ ሲ ጂ ኤም (CMA CGM) የተሰኘ ገብረሰናይ ድርጅት ለምገባ አገልግሎቱ የሚውሉ እነዚህን የመሰሉ ድጋፎች በማድረጉ በቢሮውና በተመጋቢ ተማሪዎች ስም ምስጋና አቅርበው ድርጅቱ በቀጣይም ተመሳሳይ ድጋፍ ማድረጉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል እምነታቸው መሆኑን አስታውቀዋል፡፡
የሲ ኤም ኤ ሲ ጂ ኤም(CMA CGM) ገብረሰናይ ድርጅት የኢትዮጵያ ስራአስካሄጅ አቶ ሀይሉ ተስፉ በበኩላቸው ድርጅቱ መቀመጫውን ፈረንሳይ ሀገር በማድረግ በኢትዮጵያ የተለያዩ ተግባራትን በማከናወን ላይ እንደሚገኝ ገልጸው በአዲስ አበባ በሚገኙ ትምህርት ቤቶች ላለው የተማሪዎች የምገባ አገልግሎት ድጋፍ የሚውሉ የብረት ድስቶች በመጋቢ እናቶች አማካኝነት በማቅረቡ ከፍተኛ ደስታ እንደሚሰማቸውን በትውልድ ግንባታ ሂደቱ የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነት መወጣታቸውን በመጥቀስ ድርጅታቸው በቀጣይም ከትምህርት ሴክተሩ ጋር በጋራ እንሚሰራ አስረድተዋል፡፡
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!
You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ…
TikTok፡- tiktok.com/@aaeducationbureau
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication
Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/
Website: – aaceb.gov.et
Email;- aacaebc@gmail.com
Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/