የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የስርዓተ ጾታ ማስረጽና ማካተት ዳይሬክቶሬት ለቢሮው ሴት ሰራተኞች ለሁለት ቀን የሚቆይ ስልጠና መስጠት ጀመረ፡፡
በስልጠናው የትምህርት ዝግጅታቸው የመጀመሪያ ዲግሪ እና ከዛ በላይ የሆኑ የቢሮው ሴት ባለሙያዎች የተሳተፉ ሲሆን ስልጠናውም በዋናነት ሴቶችን ወደ አመራርነት ለማምጣት የሚያስችሉ ጽንሰ ሀሳቦችን መሰረት አድርጎ የተዘጋጀ ነው፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የስርአተ ፆታ ማስረጽና ማካጸጽ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወይዘሮ አበባ ዘውዴ በስልጠናው መክፈቻ ባስተላለፉት መልዕክት የመስሪያቤታችን ሴት ባለሙያዎች ወደ ተለያዩ የአመራርነት ቦታዎች ለመምጣት ራሳቸውን በትምህርትም ሆነ ለአመራርነት ብቁ በሚያደርጉ ስልጠናዎች ማብቃት እንደሚጠበቅባቸው ጠቁመው በትምህርት ሴክተሩ የሴቶች የአመራርነት ድርሻ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱን እና በዚህ ሂደትም በሴቶች የሚመሩ ትምህርት ቤቶች አበረታች ውጤት በማስመዝገብ ላይ እንደሚገኙ አስታውቀዋል፡፡
ስልጠናውን ከከፍታ ለመድረስ የማህበረሰብና የተቃማት ስብእና ግንባታ ማዕከል የመጡት አቶ ዘላለም ይትባረክ ሴቶችን ወደ አመራርነት ማምጣት በሚል ርዕስ ያዘጋጁትን የስልጠና ሰነድ መሰረት አድርገው የሰጡ ሲሆን ሰልጣኞቹም በስልጠናው የሚነሱ ጉዳዮችን መሰረት በማድረግ በቡድን እና በጋራ በመሆን ውይይት እንደሚያደርጉ ከስልጠናው አስተባባሪዎች ያገኘነው መረጃ ያሳያል፡፡
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!
You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ…
TikTok፡- tiktok.com/@aaeducationbureau
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication
Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/
Website: – aaceb.gov.et
Email;- aacaebc@gmail.com
Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/