ኮከበ ጽበሀ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የተመሰረተበትን 90ኛ አመት በድምቀት አከበረ።
በክብረ በአሉ የትምህርት ቤቱ የቀድሞ ተማሪዎችን ጨምሮ መምህራን ወልጆች ተማሪዎችና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች የተገኙ ሲሆን በዝግጅቱ የትምህርት ቤቱን የእስካሁን ጉዞ የሚያሳይ የፎቶግራፍ አውደ ርዕይ ከመቅረቡ ባሻገር ትምህርት ቤቱ ያስገነባው የህጻናት ማቆያ /day care/ተመርቋል።
የኮከበ ጽበሀ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር አቶ ካሳሁን መኮንን በክብረ በአሉ መክፈቻ እንደገለጹት ትምህርት ቤቱ በ19 24 ዓ.ም ቀዳማዊ ሀይለ ስላሴ (ቀሀስ) ትምህርት ቤት በሚል ስያሜ ተከፍቶ የመማር ማስተማር ስራውን ሲያካሂድ ቆይቶ ከተወሰነ ጊዜ በኋላ አሁን የሚጠራበትን ስያሜ በመያዝ ላለፉት አመታት ለበርካታ ተማሪዎች የትምህርት አገልግሎት ሲሰጥ መቆየቱን ገልጸው በዚህም አያሌ የቀድሞ የትምህርት ቤቱ ተማሪዎች በተለያዩ ከፍተኛ ቦታዎች ደርሰው ሀገራቸውንና ህዝባቸውን በማገልገል ላይ እንደሚገኙ አስረድተዋል።
የመርሀ ግብሩ የክብር እንግዳና የየካ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽህፈት ቤት ተወካይ አቶ አንተነህ ዮሴፍ በበኩላቸው ትምህርት ቤቱ 90ኛ የምስረታ አመቱን በማክበሩ ለትምህርት ቤቱ ማህበረሰብና ለቀድሞ ተማሪዎች እንኳን አደረሳችሁ በማለት መልካም ምኞታቸውን ገልጸው ኮከበ ጽበሀ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በሀገራችን የትምህርት አገልግሎት መስጠት ከጀመሩ ቀደምት ትምህርት ቤቶች መካከል አንዱ መሆኑን እና ለሀገራችን የትምህርት ስርአት መሰረት የጣለ አንጋፋ ትምህርት ቤት መሆኑንም አስገንዝበዋል።
በዝግጅቱ የቀድሞ የትምህርት ቤቱ ተማሪዎች ንግግር ከማድረጋቸው ባሻገር በአሁኑ ወቅት በትምህርት ቤቱ የሚማሩ ተማሪዎች የተለያዩ የኪነጥበብ ስራዎችን አቅርበው የክብረ በአሉን ታዳሚዎች አዝናንተዋል።
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!
You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ…
TikTok፡- tiktok.com/@aaeducationbureau
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication
Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/
Website: – aaceb.gov.et
Email;- aacaebc@gmail.com
Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/