ቀን 27/5/2015 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የ2015 ዓ.ም የ6ወር እቅድ አፈጻጸሙን የተለያዩ ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ገመገመ።

በመርሀ-ግብሩ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ አመራሮችን ጨምሮ የክፍለ ከተማና ወረዳ ትምህርት ጽህፈት ቤት ኃላፊዎችና ቡድን መሪዎች፣ የመንግስትና የግል ትምህርት ቤት ርዕሳነ መምህራን፣ ሱፐርቫይዘሮች፣የመምህራን ማህበር እና የተማሪ ወላጅ ማህበር አመራሮች ተሳታፊ ሆነዋል።

በውይይቱ መክፈቻ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ ባስተላለፉት መልዕክት በ2015 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በአንደኛ መንፈቅ ዓመት በመማር ማስተማር ሂደቱ የነበረውን አፈጻጸም ከባለድርሻ አካላት በመገምገም በሁለተኛ መንፈቅ አመት የተሻለ ውጤት ማስመገብ እንዲቻል ታስቦ ውይይቱ መዘጋጀቱን ገልጸው ከብዝሀ ቋንቋ አተገባበር ጋር በተገናኘ በቅርቡ በከተማ አስተዳደሩ ካቢኔ በጸደቀው መሰረት ከጥር 29/2015 ዓ.ም ጀምሮ በትምህርት ቤቶች ተግባራዊ የሚደረግ በመሆኑ በየደረጃው የሚገኙ የትምህርት ባለድርሻ አካላት አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት ማድረግ እንደሚገባቸው አስገንዝበዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ አድማሱ ደቻሳ በበኩላቸው በ2015 ዓ.ም ግማሽ ዓመት በትምህርት ሴክተሩ ከተማሪ ቅበላ ጀምሮ የተለያዩ ተግባራት መከናወናቸውን በመጥቀስ በዋናነትም የመማር ማስተማር ስራው በቴክኖሎጂ የተደገፈ እንዲሆን መደረጉን እና አስፈላጊው የድጋፍና ክትትል ስራ መሰራቱን ጠቁመው የትምህርት ዘመኑ አዲሱ ስርዓተ ትምህርት በቅድመ አንደኛ በሙከራ ደረጃ እንዲሁም በሁሉም አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ወደ ሙሉ ትግበራ የተገባበት እንደመሆኑ በዚህ ውይይት አፈጻጸሙ እንደሚገመገም አስታውቀዋል።

በመርሀ ግብሩ የቢሮው የ6ወር እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት በእቅድና በጀት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተሩ በአቶ ጌታሁን ለማ የቀረበ ሲሆን የብዝሀ ቋንቋ የዳሰሳ ጥናት በኮተቤ ትምህርት ዩኒቨርሲቲ መምህርና ተመራማሪ በሆኑት በዶክተር ዮሴፍ ቤኮ ቀርቦ ውይይት ተካሂዶበታል።

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ

TikTok፡- tiktok.com/@aaeducationbureau

Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc

Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/

Website: – aaceb.gov.et

Email;- aacaebc@gmail.com

Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s