ቀን 26/5/2015 ዓ.ም

ለሁለት ቀናት ስናካሂድ የነበረውን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የካቢኔ አባላት የ2015 ዓ.ም የመጀመርያ ግማሽ ዓመት የስራ አፈፃፀም ግምገማ አጠናቀናል፡፡

ባለፉት ስድስት ወራት በፈታኝ ሁኔታዎች ውስጥ እያለፍንም  በርካታ ውጤታማ ስራዎች ማከናወን የተቻለበት ፤ እቅዶቻችንን ለመፈፀም  የታየው ትጋትና ተነሳሽነት አበረታችና ተስፋ ሰጪ መሆኑን ያየንበት ነበር ።

በተለይ የተቋም ሪፎርም ስራችን አገልግሎት አሰጣጡ ላይ ለውጥ የሚያመጣ ተስፋ ሰጪ ስራዎች መሰራታቸውን ብሎም የከተማዋን የኢኮኖሚ እንቅስቃሴና የስራ እድል በመፍጠር ለውጥ የሚያመጡ ታላላቅ ፕሮጀክቶች በመልካም  አፈፃፀም ላይ እንደሚገኙ ገምግመናል።

 ሆኖም አሁንም  የህዝባችንን ፍላጎትና ጥያቄዎች ለመቅረፍና የጀመርነውን ፈጣን የለውጥ ጉዞ ለማስቀጠል ከእስካሁኑ በበለጠ ጉልበታችንን አድሰን ፤ አንድነታችንን አጠናክረን ለላቀ ውጤት ልንተጋ ይገባል፡፡

ሌብነትና ብልሹ አሰራርን በቁርጠኝነት በመታገል ፣ተቋማዊ አቅም  በማጠናከር ፣የሪፎርም ስራዎችን በማከናወንና የመፈፀም አቅማችንን ከፍ በማድረግ  ለህዝባችን የተሻለ እንዲሁም የዘመነ  አገልግሎት ማቅረብ እንዳለብን አፅንኦት ሰጥተን ተመልክተናል፡፡

አዲስ አበባን አዲስና ውብ ብሎም ለነዋሪዎቿ የምትመች ፤ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን ወገኖቻችንን በላቀ ሁኔታ የምትደግፍ ፤ መረዳዳትና መደጋገፍ የሰፈነባት እንድትሆን የጀመርነውን ጥረት ከመላው ህዝባችን ጋር ሆነን አጠናክረን የምንቀጥል ይሆናል፡፡

አዲስ አበባ የሰላም የአብሮነትና የለውጥ ከተማ !!

ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን አብዝቶ ይባርክ !!

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ

TikTok፡- tiktok.com/@aaeducationbureau

Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc

Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/

Website: – aaceb.gov.et

Email;- aacaebc@gmail.com

Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s