የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች ቅሬታ ማቅረቢያ ጊዜ ነገ እንደሚያበቃ ተገለጸ፡፡
የ2014 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች ቅሬታ ማቅረቢያ ጊዜ ነገ ጥር 26/2015 ዓ.ም ከቀኑ 11፡30 ሰዓት የሚያበቃ መሆኑን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አስታወቀ።
ቀድመው ቅሬታ ያቀረቡ ተፈታኞች የቅሬታቸውን መልስ http://www.neaea.gov.et:8081 ድረ ገጽ ላይ የመለያ ቁጥራቸውን (Registration Number/ID) ብቻ በማስገባት ከዛሬ 12፡00 ሰዓት ጀምሮ ማየት የሚችሉ መሆኑን አገልግሎቱ ገልጿል።
የቀረቡ ቅሬታዎች ተጣርተው ሲጠናቀቁ የቅሬታዎቹን ምላሽ በቀጣይ ቀናት የሚያሳውቅ መሆኑን የገለጸው አገልግሎቱ ፥ የቅሬታ ምላሽ ያልደረሳችሁ ተፈታኞች በትዕግስት እንዲጠብቁ አሳስቧል።
በተመሳሳይ ያልተሟላ ወይም የተሳሳተ ወይም የሌላ ሰው መለያ ቁጥር በመጠቀም ቅሬታ ያቀረቡ ተፈታኞች የስም ዝርዝራቸውን ዛሬ ከምሽቱ 4፡00 ሰዓት ጀምሮ ከላይ በተጠቀሰው ድረ ገጽ ላይ በመመልከት ቅሬታቸውን በትክክለኛ መለያ ቁጥራቸው በድጋሚ ማቅረብ የሚችሉ መሆኑንንም ነው ያስታወቀው።
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!
You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ…
TikTok፡- tiktok.com/@aaeducationbureau
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication
Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/
Website: – aaceb.gov.et
Email;- aacaebc@gmail.com
Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/