ቀን 17/5/2015 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የስድስት ወራት እቅድ አፈፃፀም ተመዘነ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፕላን ኮሚሽን በ2015 ዓ.ም በከተማ አስተዳደሩ የሚገኙ ተቋማትን የስድስት ወራት እቅድ አፈፃፀም በመመዘን ላይ የሚገኝ ሲሆን በዛሬው እለት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በመገኘት የቢሮውን የ2015 የትምህርት ዘመን የስድስት ወራት እቅድ አፈጻጸምን መዝኗል።

በምዘናው በ2015 የትምህርት ዘመን በመጀመሪያው ስድስት ወራት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሊከናወኑ በእቅድ የተነደፉ ተግባራትን አፈጻጸም ሰነዶችን በመፈተሸ እና በአካል ወርዶ በማየት ምዘናው ተከናውናል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የእቅድ ዝግጅትና ክትትል ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ጌታሁን ለማ  ምዘናው ማስረጃ ሰነዶችን መሠረት ያደረገና በተጨባጭ ማስረጃ ላይ ተመሰርቶ መከናወኑን ገልጸዋል፡፡ አቶ ጌታሁን አክለውም  የምዘና ሂደቱ ጥሩ እንደነበር ገልፀው መዛኝ ቡድኑም መረጃዎችን በተለያዩ አማራጮች ለማረጋገጥ የሄዱበትን ርቀት አድንቀዋል።

የመዛኝ ቡድን አባላቱ በበኩላቸው በተቋሙ ያሉ የስራ መሪዎች ለምዘናው የሰጡት ግምት እና መረጃዎችን በተጠየቀው ልክ ለማቅረብ ላሳዩት ተነሳሽነት ምስጋና አቅርበዋል።

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

TikTok፡- tiktok.com/@aaeducationbureau

You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ

Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc

Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/

Website: – aaceb.gov.et

Email;- aacaebc@gmail.com

Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s