የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የትምህርት ቤት መሻሻል ዳይሬክቶሬት በተፋጠነ የትምህርት ቤት ደረጃ ማሻሻል ዙሪያ ስልጠና ሰጠ፡፡
በስልጠናው የክፍለከተማ ትምህርት ጽህፈት ቤት የትምህርት ቤት መሻሻል ቡድን መሪዎችና ባለሙያዎችን ጨምሮ ከተመረጡ ወረዳዎች የተውጣጡ የትምህርት ቤት መሻሻል ቡድን መሪዎች የተሳተፉ ሲሆን በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የትምህርት ቤት መሻሻል ባለሙያው አቶ አራጋው ዘውዴ በተፋጠነ ሁኔታ የትምህርት ቤቶችን ደረጃ ለማሻሻል የሚረዱ ሀሳቦችን የተመለከተ ጽሁፍ አቅርበው ውይይት ተካሂዳል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የትምህርት ቤት መሻሻል ባለሙያ አቶ አበበ ዘነበ እንዳስታወቁት በስልጠናው ተሳታፊ የሆኑ የክፍለከተማና የወረዳ የትምህርት ቤት መሻሻል ቡድን መሪዎችም ሆኑ ባለሙያዎች በውይይቱ ያገኙትን ግንዛቤ መሰረት አድርገው የትምህርት ቤቶች ደረጃ እንዲሻሻል ተገቢውን የድጋፍና ክትትል ስራ መስራት እንዲችሉ በማሰብ ስልጠናው መዘጋጀቱን ገልጸው ትምህርት ቤቶችም በኢንስፔክሽን ምዘና የተሰጣቸውን ግበረ መልስ መሰረት በማድረግ ደረጃቸውን ማሻሻል እንደሚገባቸው አስገንዝበዋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የትምህርት ቤት መሻሻል ባለሙያ አቶ ሳሙኤል አየለ በበኩላቸው ከሶስት አመቱ ስትራቴጂክ እቅድ ዝግጅት ጋር በተገናኘ የታዩ ክፍተቶችን መነሻ በማድረግ ማስተካከያዎች መሰጠታቸውን ገልጸው ትምህርት ቤቶች የህብረተሰቡን ተሳትፎ በማሳደግም ሆነ ሌሎች አማራጮችን በመጠቀም የውስጥ ገቢያቸውን አሳድገው የትምህርትቤቶቻቸውን ደረጃ መሻሻል እንዲችሉና የሚመደብላቸውን የድጎማ በጀት ለታለመለት አላማ ማዋላቸውን የክፍለከተማና የወረዳ የትምህርት ቤት መሻሻል ቡድን መሪዎችም ሆኑ ባለሙያዎች አስፈላጊውን የድጋፍና ክትትል ስራ በመስራት ማረጋገጥ እንደሚገባቸው አስረድተዋል፡፡
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!
TikTok፡- tiktok.com/@aaeducationbureau
You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ…
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication
Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/
Website: – aaceb.gov.et
Email;- aacaebc@gmail.com
Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/