ቀን 3/5/2015 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የ2015 ዓ.ም ትምህርት ዘመን የ6 ወራት እቅድ አፈፃፀምን ከቢሮ ሰራተኞች ጋር ገመገመ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ዳኛው ገብሩ ሪፖርቱ በማኔጅመንት እና በፕሮሰስ ካውንስል መታየቱን ጠቁመው በዝግጅት ምእራፍ በ2014 በጀት ዓመት የታዩ ጥንካሬዎች ለማስቀጠል በ2015 አይቀጥሉም ተብለው የተቀመጡ ጉድለቶችን ለማረም አቅደን የገባን በመሆኑ በአፈፃፀም የተደረጉ ጥረቶች የተሻሉ ነበሩ ብለዋል:: አቶ ዳኘው አክለውም የተገኙ ውጤቶች ከቢሮ እስከ ትምህርት ቤት ባሉ አካላት የጋራ ርብርብና ጥረት የተገኘ ነው ብለዋል::

በዕለቱ አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የ2015 ዓ.ም ትምህርት ዘመን የ6 ወራት እቅድ አፈፃፀም ከአስር ዋና ዋና ግቦች አንፃር በየዳይሬክቶሬቱ የተከናወኑ ተግባራት እቅድ እና የትስስር ሰነድ አፈፃፀም ሪፖርት በእቅድና በጀት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር በሆኑት በአቶ ጌታሁን ለማ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል::

በሪፖርቱ በግማሽ ዓመት እንደ ቢሮ የተከናወኑ ዋና ዋና ሥራዎች ያጋጠሙ ችግሮችና የመፍትሄ ሃሳቦች እንዲሁም በበጀት ዓመቱ ቀሪ ወራት ሊከናወኑ የሚገቡ የትኩረት አቅጣጫዎች ቀርበዋል::

በተጨማሪም በመድረኩ በበጀት ዓመቱ ከቢሮ እስከ ትምህርት ቤት ድረስ የተለዩ የመልካም አስተዳደር ችግሮች የስድስት ወራት አፈጻጸም ሪፖርት በቢሮ ጽፈት ቤት ሀላፊ በሆኑት በአቶ ሲሳይ እንዳለ የቀረበ ሲሆን በሪፐርቱም ከተለዩ 11 የመልካም አስተዳደር ችግሮች 7ቱ የተፈቱ ፣ 3ቱ በሂደት ላይ ያሉ እና አንድ ችግር ያልተፈታ ችግር መሆኑን በሪፖርቱ ላይ  ተገልጽዋል፡፡

የቀረበውን ሪፖርት መሰረት በማድረግ ያልተካተቱ ነጥቦች ማብራሪያ የሚፈልጉ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ከተሳታፊዎች ተነስተው ምላሽ ተሰጥቷቸዋል ::

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

TikTok፡- tiktok.com/@aaeducationbureau

You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ

Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc

Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/

Website: – aaceb.gov.et

Email;- aacaebc@gmail.com

Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s