ቀን 28/4/2015 ዓ.ም

ሊቃውንት እንዳስተማሩን እግዚአብሔር አምላክ ዓለምን ከፈጠረበት ጥበቡ ይልቅ ዓለምን ያዳነበት ጥበቡ ይበልጣል፡፡ ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተወለደበት እና ዓለምን ያዳነበት ምሥጢር ከምሥጢራት ሁሉ በላይ ነው፡፡ ይህን ምሥጢር ከማድነቅ ሌላ ሊናገሩት አይቻልም፡፡

እንኳን ለዚህ ታላቅ ቀን ለእየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ! አደረሰን!

ትውልድን የመቅረጽ ስራ ልዩ ትኩረትን እና ትጋትን የሚጠይቅ ታላቅ ስራ ነው፡፡ ለዛም ነው እስካሁን የሰራናቸው ውጤታማ የትምህርት ልማት ስራዎቻችን ያጎናጸፉን ድል እንዳለ ሆኖ ከምንጊዜውም በላይ ዛሬ የምናከናውናቸው የትምህርት ልማት ስራዎቻችን የላቀ ውጤት እንዲመዘገብ በማድረግ ረገድ ከፍያቸው የምንኮራበት እንደሚሆን ደከመኝ ሰለቸኝ ሳንል በትጋት ልንሰራ የሚገባው፡፡

ተማሪዎች አዳዲስ ነገሮችን መስራት እና ማበልፀግ እንዲችሉ ብቁ ማድረግ የምንችለው ተማሪዎች ለትምህርታቸው  ትኩረት እንዲሰጡ ማድረግ ስንችል ነው፡፡ ለዚህ መሳካት ደግሞ የመምህራን ፣ የትምህርት አመራሮች ፣ ባለሙያዎች እና የትምህርት ባለድርሻ አካላት ሚና ትልቅ በመሆኑ አሰካሁን ላደረጋችሁት አበርክቶ መስጋናዩን እያቀረብኩ በቀጣይ ለምንሰራቸው ስራዎች ውጤታማነት በተለይም ደግሞ ሰላማዊ መማር ማስተማር እንዲረጋገጥ የሚጠበቅባችሁን ሁሉ እንድታደርጉ እንዲሁም ተማሪዎች ለትምህርታችሁ ትኩረት በመስጠት ቤተሰቦቻችሁ እና የከተማ አስተዳደሩ ከጎናችሁ በመሆን እያደረጉላችሁ ለሚገኙት ድጋፎች የተሻለ ውጤት በማስመዝገብ ኩራት እንድትሆኑ አደራ ልላችሁ እወዳለሁ፡፡

በመጨረሻም በክርስትና እምነት ተከታዮች የሚከበረውን ይህንን የእየሱስ ክርስቶስ ልደት በዓልን ስናከብር የተቸገሩ ወገኖቻችንን በመርዳት ፣ ያለንን በማካፈል ፣ አቅመ ደካሞችን በማገዝ እና መዓድ በማጋራት በመተሳሰብ መንፈስ ሊሆን ይገባል፡፡

እንኳን ለእየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ! አደረሰን!

በዓሉ የሠላም ፣ የመተሳሰብ እና የፍቅር እንዲሆን እመኛለሁ

አመሰግናለሁ!

ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ ደሙ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

TikTok፡- tiktok.com/@aaeducationbureau

You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ

Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc

Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/

Website: – aaceb.gov.et

Email;- aacaebc@gmail.com

Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s