ቀን 28/4/2015 ዓ.ም

አዲስ አበባ የሁላችንም ከተማ በሚል መሪ ቃል ከተማ አቀፍ የፅዳት ንቅናቄ ተካሄደ፡፡

በዛሬው እለት በአዲስ አበባ ‹‹አዲስ አበባ የሁላችንም ከተማ›› በሚል መሪ ቃል ከሁሉም የህብረተሰብ ክፍሎች የተውጣጡ የከተማዋ ነዋሪዎች የተሳተፉበት የፅዳት ንቅናቄ ተካሄደ፡፡

የዓለም የዲፕሎማሲ ማዕከል የሆነችውን አዲስ አበባ ከተማን ከከፋፋይ አስተሳሰቦችና ቆሻሻ በማጽዳት ለስራና ለኑሮ የተመቸች ውብ ከተማ ማድረግ እንደሚገባ  በዚህ ፕሮግራም ላይ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለፀዋል፡፡

የገና በዓልን ምክንያት በማድረግ የከተማው አመራሮች የሀይማኖት አባቶች፣ዲፕሎማቶች የስፖርት ቤተሰብ አባላት የእግር ኳስ ክለቦች ደጋፊዎች፣ ስፖርተኞች ፣መምህራን፣ተማሪዎች እና ነዋሪዎች የጤና ባለሙያዎች የፅዳት ባለሙያዎች፤ የኪነጥበብ ሰዎች  በተገኙበት ተካሄዷል፡፡

የቱሪስት መተላላፊያ ሆና ቆየችውን አዲስ አበባ ከተማን የቱሪስት መዳረሻ ለማድረግ በርካታ ስራዎች እየሰራን ያሉት ከንቲባዋ በትልቅነቷ ልክ በጋራ መስራትና ፍትሀዊ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ ከተማ አስተዳደሩ ተግቶ እየሰራ መሆኑን ገለጸዋል፡፡

ከንቲባ አዳነች አቤቤ የከተማዋን ዕድገት የሚያፋጥኑ ስራዎች እየተሰሩ መሆናቸውን ገልጸው ከተማዋ ያሏትን ጸጋዎችን በመጠቀም ለነዋሪዎቿ ፍትሀዊ ተጠቃሚነት በጋራ መስራት እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡

ብዙዎች ስለአዲስ አበባ ከተለያዩ አካባቢዎች ብዙዎች ሲቆረቆሩ እየተመለከትን ነው ያሉት ከንቲባ አዳነች በዚህም እኛ ደስተኛ ነን ያሉ ሲሆን  ነዋሪዎቿ  ደግሞ ስለ ከተማቸው ማሰብና ማድረግ የሚችሉ መሆናቸውንና በመተባበር አዲስ አበባን እንደሚያሳድጉ ገልፀዋል፡፡

ከንቲባ አዳነች በዓይን የሚታየውን ቆሻሻ እያጸዳን የማይጠቀመውን ከፋፋይ አስተሳሰብ በማጽዳት ሰላማችንን መጠበቅም ይገባል ብለዋል፡፡

በተጨማሪም የከተማችን የሚያጋጥሙንን ጥቄዎችን  በሰለጠነ መንገድ በማቅረብ መነጋገርና መግባባት በተግባባንበት በጋራ ተግባራዊ ማድረግ እንደሚገባ የገለጹት ከንቲባ አዳነች የአዲስ አባባ ልጆች ይህን በማድረግ ለከተማዋ ሰላም የበኩላቸውን በመወጣት ለሌሎች ሀገራችን አካባቢዎች ምሳሌ እንደሚሆኑ ያላቸውን ዕምነት ገልፀዋል፡፡

አቶ ጥራቱ በየነ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ሥራ አስኪያጅ በበኩላችው ከተማ አስተዳደሩ ከሕዝቡ ጋር በመቀናጀት በሰራቸው ስራዎች አዲስ አባባ መጽዳትና መዋብ ከመቻሏ በተጨማሪ በቆሻሻ መሰብሰብና መልሶ መጠቀም ዘርፍ የተሰማሩ ወጣቶች ገቢ ማግኘት መጀመራቸውን ገልጸዋል፡፡

በተሰሩት ስራዎች የተገኙ ውጤቶችና ዓለም አቀፍ ዕውቅናዎች ዘላቂ መሆን የሚችሉት ከተማችንን በምናጸዳበትና በምናስውብበት ልክ የህዝቡን አብሮ የመኖር እሴት የሚጎዱ የተዛቡ አስተሳሰቦች በጋራ በማጽዳት መሆን እንዳለበት አቶ ጥራቱ ገልጸዋል፡፡

በማለዳ ወጥተው ከተማ የሚያጸዱ፣ ቤት የሚያድሱ የሚገነቡ፣ የከተማቸው  ሰላም ለማስከበር በሰላም ሰራዊት ራሳቸውን ያደራጁ እና በምግባ ማዕከላት ማዕድ የሚያጋሩ በጎ ፈቃደኞች  ባሉባት ከተማ ስራ የማይሰሩ ጥቂት ግለሰቦች ከፋፋይ አመለካከቶች ማራገባቸው ለብልጽግናችን የማይበጁ በመሆናቸው በጋራ ማስቆም  አስፈላጊ መሆኑን አቶ ጥራቱ አሳስበዋል፡፡

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

TikTok፡- tiktok.com/@aaeducationbureau

You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ

Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc

Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/

Website: – aaceb.gov.et

Email;- aacaebc@gmail.com

Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s