የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በአዲሱ የተቋሙ አዳረጃጀት መመሪያ ዙሪያ ላይ ለሰራተኞች ኦረንቴሽን ሰጠ።
ኦረንቴሽኑ መዋቅሩን ባጠኑ ኮሚቴዎች የተሰጠ ሲሆን አደረጃጀቱም አዋጅ ቁጥር 74/2014 መሰረት አድርጎ መዘጋጀቱን በኮሚቴዎች ከመገለጹ ባሻገር መዋቅሩም በፐብሊክ ሰርቪስ ቢሮ ጸድቆ መምጣቱ ተጠቁሟል።
በመርሀ ግብሩ መክፈቻ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሲሳይ እንዳለ እንዳስታወቁት መዋቅሩ ለውጡን ተከትሎ ከተማ አስተዳደሩ ለህዝቡ የሚሰጠውን አገልግሎት ቀልጣፋና ውጤታማ እንዲሆን በማሰብ በአዲስ መልክ እንዲጠና መደረጉን ገልጸው የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮም በየደረጃው የሚሰጠውን አገልግሎት ውጤታማ ማድረግ እንዲችል የሚረዳ አደረጃጀት ልምድ ባላቸው የትምህርት ባለሙያዎች ማስጠናቱን አስረድተዋል።
የጽህፈት ቤት ኃላፊው አክለውም ቢሮው ጥናቱን በሚፈልገውና አጥኚ ቡድኑ ባጠናው መሰረት አዳዲስ የስራ ክፍሎችን በማደራጀት ማጸደቁን ጠቁመው የቢሮው ባለሙያዎችም በመመሪያው መሰረት ስራልምዳቸውም ሆነ የትምህርት ዝግጅታቸው በሚጋብዛቸው መደብ መወዳደር እንደሚገባቸው አስገንዝበዋል።
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!
TikTok፡- tiktok.com/@aaeducationbureau
You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ…
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication
Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/
Website: – aaceb.gov.et
Email;- aacaebc@gmail.com
Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/