ቀን 25/4/2015 ዓ.ም

ሰራተኞች በቢሮው የማህበራዊ ኮሚቴ እና የገንዘብ ቁጠባና ብድር ስራዎች ላይ ውይይት አካሄዱ፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሰራተኞች የተቋቋመው የሰራተኞች ማህበራዊ ኮሚቴ እንቅስቃሴ ላይ እና በሰራተኞች የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃላፊነቱ የተወሰነ የህብረት ስራ ማህበር ስራዎች ላይ ውይይት ተካሄዳል፡፡

በውይይቱ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ሀላፊ አቶ ዳኛው ገብሩ ሰራተኞችን እንኳን ለእየሱስ ከርስቶስ ልደት በዓል /ለገና በዓል/ አደረሳችሁ በማለት ሰራተኛው በቢሮው ውስጥ በተቋቋሙ ማህበራዊ መስተጋብሮችን በሚያጠናክሩ መስል ተግባራት ላይ በንቃት መሳተፉ ጠቀሜታው የጎላ ከመሆኑ በተጨማሪ  ቁጠባን ባህሉ በማድረግ ለላቀ ውጤት መትጋት ይጠበቅበታል ብለዋል፡፡

የቢሮ ማህበራዊ ኮሚቴ የስራ ሪፖርት በኮሚቴው ሰብሳቢ በአቶ መክብብ በለጠ እንዲሁም የአዲስ አበበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ  የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃላፊነቱ የተወሰነ የህብረት ስራ ማህበር አገልግሎትን የማህበሩ ሂሳብ ሹም በሆኑት በአቶ ግሩም አስማረ ቀርቦ ውይይት ተካሂዶበታል፡፡

በውይይቱ የተካፈሉ የቢሮ ስራተኞች በበኩላቸው ሰራተኞች እርስ በእርስ እንዲቀራረቡ እና ለጋ አላማ በእንድነት ለመሰለፍ እንዲችሉ እንዲህ አይነት ማህበራዊ አገልግሎት የሚሰጡ እንቅስቃሴዎች ላይ መሳተፍ ጠቀሜታው ከፍተኛ በመሆኑ ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ብለዋል፡፡

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

TikTok፡- tiktok.com/@aaeducationbureau

You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ

Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc

Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/

Website: – aaceb.gov.et

Email;- aacaebc@gmail.com

Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s