ቀን 22/4/2015 ዓ.ም

የተማሪ ወላጆች በብዝሀ ቋንቋ አተገባበር ጥናት ላይ ተወያዩ፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ በሁሉም ክፍለ ከተሞች የሚገኙ የተማሪ ወላጆች ከአፍ መፍቻ ተጨማሪ የሀገር ውስጥና የውጪ ቋንቋዎችን በትምህርት ስርዓቱ ለማካተት የኮተቤ ትምህርት ዩኒቨርስቲ ባደረገው የብዝሀ ቋንቋ አተገባበር ጥናት ላይ ተወያይተዋል።

የብልፅግና ፓርቲ አዲስ አበባ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ መለሰ ዓለሙ በየክፍለ ከተማው በውይይቱ ለተሳተፉ የተማሪ ወላጆች በቪዲዮ ኮንፈረንስ ባስተላለፉት መልዕክት ኢትዮጵያ ብዝሀነቷን አክብራና ተንከባክባ ከትውልድ ትውልድ እንድትሸጋገር የተለያዩ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን አንስተዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ የትምህርት ስርዓቱ በዋናነት ሊተገብረው የሚገባው ጉዳይ ለነገው ትውልድን የማነፅና የሀገር ግንባታ እንዲሁም ለልጆቻችን የተሻለች ሀገርን መፍጠር ነው ሲሉ ተናግረዋል::

ለብዝሀ ቋንቋ አተገባበር ኮተቤ ዩኒቨርስቲ ያደረገው ጥናትም ህብረብሔራዊ አንድነታችንን ለማጠናከር የራሱ ድርሻ እንደሚኖረው በማስረዳት ወላጆች የሚሰጧቸው ሀሳቦች ለብዝሀ ቋንቋ አተገባበሩ እና ለመማር ማስተማሩ ሂደት ስኬታማነት እንደ ተጨማሪ ግብአት እንደሚወሰዱ አቶ መለሰ ተናግረዋል።

የብዝሀ ቋንቋ አተገባበርን የጥናት ውጤት ያቀረቡት የኮተቤ ትምህርት ዩኒቨርስቲ መምህር ዶ/ር ዮሴፍ ተማሪዎች፣ መምህራንና ወላጆች በጥናቱ ወቅት ግብአት መስጠታቸውን ገልፀው የዛሬው ውይይትም ከቅርበት፣ ከተደራሽነት፣ ከተጠቃሚነት እንዲሁም ከማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና አስተዳደራዊ ጉዳዮች አንፃር የጥናቱ ውጤት ምን እንደሚመስል ከወላጆች ጋር የጋራ ለማድረግና በተጨማሪ ግብአት ለማዳበር መሆኑን አስረድተዋል።

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

TikTok፡- tiktok.com/@aaeducationbureau

You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ

Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc

Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/

Website: – aaceb.gov.et

Email;- aacaebc@gmail.com

Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s