በብዝሀ ቋንቋ ዙርያ በተጠና የጥናት ውጤት ላይ ውይይት ተደረገ፡፡
የጉለሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር አመራሮች በብዝሀ ቋንቋ ዙርያ በተጠና የጥናት ውጤት ላይ ውይይት አደረጉ።
ለብዝሀ ቋንቋ አተገባበር ከአፍ መፍቻ ቋንቋ በተጨማሪ የሀገር ውስጥና የውጪ ቋንቋዎችን በስርዓተ ትምህርት ለማካተት የኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርስቲ ባደረገው የጥናት ውጤትም ላይ ውይይት ተደርጓል።
ብዝሀ ቋንቋ ማወቅ የህዝብ ፍላጎት ቢሆንም የአለም አቀፍና የሀገር ውስጥ ልምምድን ማየትና በጥናት መመለስ አስፈላጊ በመሆኑ የከተማ አስተዳደሩ ሀላፊነት ወስዶ ለሀገር ግንባታ የሚጠቅም ስራ እየሰራ መሆኑን ማሳያ እንደሆነ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ ገልጸዋል።
በተመሳሳይ የክፍለ ከተማው ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ተስፋዬ ኦሜጋም ብዝሀ ቋንቋ ማወቅ ለአለም ሰው ልጆች ሁሉ በጣም አስፈላጊ ነው ብልጽግና ፓርቲ ሰው ተኮር በመሆኑ ፍላጎቱን ለማሟላት የሚሰራ መሆኑን ማሳያ ነው።ጥናቱ እየገነባን ላለነው ሁሉን አቃፊ የበለጸገች ኢትዮጵያ አስፈላጊ ውጤት ይዞ የመጣ መሆኑንና አመራሩ ለተግባራዊነቱ የራሱን ሚና መወጣት እንደሚገባው መግለጻቸውን ከጉለሌ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ የሳያል።
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!
TikTok፡- tiktok.com/@aaeducationbureau
You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ…
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication
Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/
Website: – aaceb.gov.et
Email;- aacaebc@gmail.com
Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/