ቀን 18/4/2015 ዓ.ም

በብዝሀ ቋንቋ ዙርያ በተጠና  የጥናት ውጤት ላይ ውይይት ተደረገ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ አመራሮች አስተዳደሩ ለብዝሀ ቋንቋ አተገባበር ከአፍ መፍቻ በተጨማሪ የሀገር ውስጥና የውጪ ቋንቋዎችን በስርዓተ ትምህርት ለማካተት የኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርስቲ ባደረገው የጥናት ውጤት ላይ ውይይት ተደርጓል።

የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ጥናቱ ከባለፈው ዓመት መጋቢት ወር ጀምሮ ሲደረግ መቆየቱን ጠቅሰው በተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች በውይይት እየዳበረ መሆኑን አስረድተው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ አመራሮችም በግልፀኝነት ተወያይተውበት  በቀጣይ ህዝቡን ማወያየት እንደሚያስፈልግ አስረድተዋል::

የጥናት ፅሁፉን ያቀረቡት የኮተቤ ዩኒቨርስቲ መምህር ዶ/ር ዮሴፍ ከአንድ በላይ ቋንቋዎችን ማወቅ ከሚያስገኘው ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ በተጨማሪ ማህበራዊ መስተጋብርንና ትስስርን የማጠናከር እና ሌሎች ፍልስፍናዊና ባህላዊ እውቀቶችን እንደሚያጎናፅፍ፤ በአገራችንም በተለይም ኦሮሚያ ክልል ከሌሎች ክልሎች ጋር በሚዋሰንባቸው አካባቢዎችና በሌሎችም ክልሎች የተጀማመሩ ስራዎች ያስገኟቸውን መልካም ውጤቶች በመጥቀስ አብራርተዋል።

በተደረገው ጥናት ከአገር ውስጥ ቋንቋዎችና ከእንግሊዝኛ በተጨማሪ ከቅርበት ከተደራሽነት እና በሌሎች ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ምክንያቶች ሌሎች የአካባቢው ቋንቋዎችንም ለመማር ምርጫቸው መሆኑ በጥናቱ መረጋገጡ ቀርቧል።

ጥናቱ የተማሪዎችን፣ የመምህራንንና የወላጆችን ሀሳብ ያካተተ ለምሁራን ቀርቦ በተጨማሪ ግብዓት የዳበረና በቀጣይም የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችም በውይይታቸው የበለጠ የሚያዳብሩት መሆኑ ተገልጿል።

በውይይቱ የተሳተፉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አመራሮችም  ለብዝሀ ቋንቋ አተገባበር ከአፍ መፍቻ በተጨማሪ የሀገር ውስጥና የውጪ ቋንቋዎችን  መማር የጥናት ውጤትም መሬት ላይ ያለውን እውነታ ያረጋገጠ መሆኑንና  የቀጣዩ ትውልድ ማህበራዊ ትስስር የበለጠ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ብዝሀ ቋንቋ  አተገባበር ፋይዳው የጎላ መሆኑንም አስረድተዋል።

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

TikTok፡- tiktok.com/@aaeducationbureau

You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ

Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc

Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/

Website: – aaceb.gov.et

Email;- aacaebc@gmail.com

Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s