ቀን 15/4/2015 ዓ.ም

የ2015 ዓ.ም የውስጥ ስፖርታዊ ውድድር በእቴጌ መነን የልጃገረዶች አዳሪ ት/ቤት ተጀመረ፡፡

በስፖርታዊ ውድድሩ አጀማር ስነ-ስርዓት ላይ የት/ቤቱን ማህበረሰብ በስፖርታዊ የውድድር ፕሮግራሞች አማካኝነት የእርስ በእርስ ግንኙነትን ወዳጅነትንና አንድነትን እንዲያጠናክር ንቁ ጤናማና ውጤታማ ማህበረሰብ እንዲሆኑ የስፖርታዊ ፕሮግራሞች ማስፈፀሚያ ማንዋል በማዘጋጀት በ2013 ዓ.ም ወደ ትግበራ የተገባ መሆኑ ተገልጻል፡፡

በስፖርታዊ ውድድሩ የት/ቤቱ እና የአቻ ት/ቤት አመራሮች፤ መምህራንና ተማሪዎች ታድመዋል፡፡

በዚህ ስፖርታዊ ውድድር ስነ-ስርዓት ላይ የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ያደረጉት የእቴጌ መነን የልጃገረዶች አዳሪ ት/ቤት ርዕሰ መምህርት ወ/ት ሃና ፀጋዬ የስፖርታዊ ውድድሮች ጤናማ ማህበረሰብ ለመፍጠር የሚጫወቱት ሚና ከፍተኛ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የገላን የወንዶች 2ኛ ደረጃ አዳሪ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር አቶ ካሳሁን መርጋለተወ ዳዳሪ መምህራንና ተማሪዎች መልካም የውድድር ጊዜ ተመኝተዋል፡፡

በዚህ ስፖርታዊ ውድድር መምህራንና የተማሪዎች በሁለት ምድብ የሚሳተፉ ሲሆን እያንዳንዱ ምድብ በስሩ የቮሊቮል፤ የእግር ኳስ፤ የእሩጫ፤ የቴብል ቴንስ እና የገመድ ጉትቻ ውድኖች ይኖሩታል፡፡

በመክፈቻ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ ልዩ ልዩ ስፖርታዊ ትዕይንቶች በተማሪዎች የቀረቡ ሲሆን በዕለቱ የመጀመሪያው ውድድር የሆነው በካኔኑስ እና በሉሲ የሴት ተማሪዎች የእግር ኳስ ቡድኖች መካከል የተደረገው ውድድር ነው፡፡ 

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

TikTok፡- tiktok.com/@aaeducationbureau

You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ

Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc

Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/

Website: – aaceb.gov.et

Email;- aacaebc@gmail.com

Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s