የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የስርአተ ጾታ ማስረጽና ማካተት ዳይሬክቶሬት የፀረ ጾታዊ ጥቃት ጥቃት ቀን ወይም የነጭ ሪቫን ቀንን የቢሮው ሰራተኞት በተገኙበት አከበረ።
ቀኑ ዘንድሮ ሴትን አከብራለሁ ጥቃቷንም እከላከላለሁ በሚል መሪ ቃል በአለም አቀፍ ደረጃ ለ31ኛ እንዲሁም በሀገራችን ደግሞ ለ17ኛ ጊዜ ከህዳር 16 ጀምሮ በተለያዩ መርሀ ግብሮች ሲከበር መቆየቱ ተገልጿል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሲሳይ እንዳለ በመርሀ ግብሩ ባስተላለፉት መልዕክት ቀኑ ሴቶች ላይ የሚደርስን ጥቃት ለመከላከል በማሰብ በተለይም በወንዶች የሚከበር እንደመሆኑ በሴቶች ላይ የሚደርስ ማን ኛውንም ጥቃት በመከላከል የሀገርን ሁለንተናዊ እድገት ማስቀጠል እንደሚገባ ጠቁመው የትምህርት ማህበረሰቡም ሆነ ጉዳዩ የሚመለከተው ማን ኛው ባለድርሻ አካል በትምህርት ተቋማት የሚስተዋሉ ጾታዊ ጥቃቶችን ለመከላከል በሚደረገው እንቅስቃሴ የበኩላቸውን ኃላፊነት መወጣት እንደሚጠበቅባቸው አስረድተዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የስርአተ ጾታ ማስረጽና ማካተት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወይዘሮ አበባ ዘውዴ በበኩላቸው የነጭ ሪቫን ቀን እ.አ.አ ታህሳስ 1989 ዓ.ም ካናዳ ሞንትሪያል ከተማ በአንድ ወጣት ወንድ 14 ሴት ተማሪዎችን አስከፊ በሆነ መልኩ መገደላቸውን መሰረት በማድረግ እ.አ.አ ከ19 91ዓ.ም ጀምሮ ወንዶች ሴቶች ላይ የሚደርሱ ጥቃቶችን በመቃወም የሚከበር መሆኑን ገልጸው ጾታዊ ጥቃትን ከመከላከል አንጻር የወንዶች ሚና ከፍተኛ በመሆኑ ጥቃቱን ማውገዝና መከላከል እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
በመርሀ ግብሩ ማጠቃለያ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ዳኘው ገብሩ ባስተላለፉት መልዕክት ቀኑ ሴቶች ላይ የሚደርስ ማንኛውንም ጥቃት ከአስተሳሰብ ጀምሮ በማውገዝና በመከላከል ተግባራዊ እንቅስቃሴ ማድረግ እንደሚገባ አስታውቀዋል።
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!
TikTok፡- tiktok.com/@aaeducationbureau
You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ…
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication
Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/
Website: – aaceb.gov.et
Email;- aacaebc@gmail.com
Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/