በአዲስ አበባ ከተማ ባሉ አንዳንድ ትምህርት ቤቶች ተከስቶ የነበረው የፀጥታ ችግር ተረጋግቶ የመማር ማስተማሩ ሂደት በሰላም እየተከናወነ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ፡፡
ባለፈው ሰሞን በአንዳንድ ትምህርት ቤቶች ላይ ባንዲራና መዝሙርን ሽፋን በማድረግ አጋጥሞ የነበረው የፀጥታ ችግር ተቀርፎ የመማር ማስተማሩ ሂደት በሠላም እየተከናወነ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል ፡፡
መምህራን ፣ ወላጆች እና በየደረጃው የሚገኙ የትምህርት ቤት አመራሮችን በልዩ ልዩ መድረኮች ማወያየት በመቻሉ እና የፀጥታና የደህንነት የጋራ ግብረ ሀይሉ ከልዩ ልዩ ባለድርሻ አካላት ጋር ባከናወነው የተቀናጀ ሥራ በትምህርት ቤቶች ላይ አጋጥሞ የነበረውን የፀጥታ ችግር መቅረፍ እንደተቻለ ገልጿል ፡፡
በትምህርት ቤቶች ውስጥ ዘላቂ ሰላም ለማምጣት ለልዩ ልዩ አካላት ከሚሰጠው የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራ ጎን ለጎን የመማር ማስተማሩ ሂደት ፍፁም ሰላማዊ ሆኖ እንዲቀጥል ህግ የማስከበር ስራው ተጠናክሮ መቀጠሉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ገልፆል፡፡
ባለፈው ጊዜ አጋጥሞ በነበረው የፀጥታ ችግር ላይ ድብቅ አጀንዳቸውን ለማራመድ ሲንቀሳቀሱ በተገኙ አካላት ላይም በህግ አግባብ እርምጃ የተወሰደ ሲሆን በስሜት በመነዳት እና ባለማወቅ የፀረ-ሰላም ኃይሎች መጠቀሚያ የሆኑ አብዛኛው ተማሪዎች አስፈላጊው ምክር ተሰጥቷቸው መለቀቃቸውን ተገልፆል፡፡
ሰላምና ደህንነትን የማስጠበቅ ኃላፊነት ለፀጥታ አካላት ብቻ የሚተው ተግባር ባለመሆኑ ህብረተሰቡ ህገ-ወጥ ድርጊት ሲያጋጥም ፈጥኖ ጥቆማ የመስጠት ልምዱን አጠናክሮ እንዲቀጥል እና ፀረ-ሰላም ኃይሎች ተማሪዎችን የአጀንዳቸው ማራመጃ እንያዳደርጓቸው ወላጆች ልጆቻቸውን መከታተል፣ መምከርና መቆጣጠር እንዳለባቸው የአዲስ አበባ ፖሊስ መልእክቱን አስተላልፏል፡፡
የፀጥታ አካላት የህብረተሰቡን ሰላምና ደህንነት የማረጋገጥ ኃላፊነት እንዳለባቸው ፖሊስ አስታውቆ ግጭትን የፖለቲካ ትርፍ ማሳኪያ መንገድ በማድረግ የህብረተሰቡን አብሮነት የሚሸረሽሩ ተግባራት ላይ የተሰማሩ ፀረ-ሰላም ኃይሎች ሁኔታዎች በተረጋጉበት እና የመማር ማስተማሩ ሂደት ሰላማዊ በሆነ ሁኔታ እየተካሄደ ባለበት በአሁኑ ወቅት የታሰሩ ተማሪዎች አልተለቀቁም የሚል የተዛቡ መረጃዎችን እያሰራጩ ነው፡፡
በታችኛው ፍ/ቤት በዋስ እንዲፈቱ የተወሰነላቸውን ግለሰቦች መብትን ፖሊስ የማክበር ግዴታ ያለበት ቢሆንም በህጉ መሰረት የስር ፍ/ቤት በሰጠው የዋስትና ጉዳይ ላይ ይግባኝ የማለት ኃላፊነት እንዳለው እየታወቀ ፖሊስ የፍ/ቤትን ትእዛዝ አላከበረም የሚል መረጃ በአንዳንድ ማህበራዊ ሚዲያዎች መሰረጨቱ ተገቢ አለመሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ እያስታወቀ አሁንም የሚመለከታቸውን አካላት ሳይጠይቁ የተዛባ መረጃ የሚያሰራጩ አካላት ከድርጊታቸው ሊቆጠቡ ይገባል ብሏል፡፡
በልዩ ልዩ መንገዶች የትምህርት ቤቶችን ፀጥታ ለማደፍረስ በሚንቀሳቀሱም ሆነ በተለይ የተዛባ ሀሰተኛ መረጃ የሚያሠራጩ አካላት ላይ የአዲስ አበባ ፖሊስ እያደረገ ያለውን ጥብቅ ቁጥጥር በማጠናከር አጥፊዎችን ህግ ፊት የማቅረብ ተግባሩን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቋል፡፡
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!
TikTok፡- tiktok.com/@aaeducationbureau
You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ…
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication
Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/
Website: – aaceb.gov.et
Email;- aacaebc@gmail.com
Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/