በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አዲስ የተጠናው የብዝሃ ቋንቋ ካሪኩለም በዚህ ሳምንት ውይይት የሚካሄድበት መሆኑ ተገለጸ፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በየደረጀው ከሚገኙ የትምህርት ማህበረሰብ አካላት ጋር የጀመረውን ውይይት አጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን በሌላ በኩል በዛሬው እለት በሁሉም ክ/ከተሞች በትምህርት ቤቶች የተረጋጋ እና ሰላማዊ የመማር ማስተማር ሂደት በመካሄድ ላይ ይገኛል፡፡
የከተማ አስተዳደሩ እያካሄደው ባለው በዚሁ ውይይት ላይ የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ ሃላፊ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ እንደገለፁት የከተማ አስተዳደሩ ከነሃሴ 2014 ጀምሮ በኮተቤ ዩንቨርሲቲ ሲያስጠናው የቆየውን የቋንቋ ካሪኩለም አጠናቆ በዚህ ሳምንት ለውይይት እንደሚያቀርብ አስታውቀዋል፡፡
ይህ ካሪኩለም ፀድቆ ወደ ትግበራ የሚገባና በተለይም የከተማዋን ብዝሃነት በብቃት የሚያስተናግድ ስርዓት የሚተገበር መሆኑን የገለፁት ዶ/ር ዘላለም በተለይም በሀገራችን አዲሱ የቋንቋ ትምህርት ፖሊሲ መሰረት 3 ቋንቋዎችን ራሳቸውን ችለው እንደ አንድ የትምህርት አይነት በትምህርት ቤቶች እንዲሰጡ ለማድረግ እና የባንዲራ እና የመዝሙሩም ጉዳይም መፍትሄ የሚሰጥ መሆኑንም ሃላፊው ጠቁመዋል፡፡
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!
TikTok፡- tiktok.com/@aaeducationbureau
You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ…
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication
Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/
Website: – aaceb.gov.et
Email;- aacaebc@gmail.com
Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/