ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በአሜሪካ “የአፍሪካ የላቀ የአመራር” ሽልማት ተሸለሙ
“አፍሪካ፡ የዓለም አቀፍ ንቅናቄ አጣዳፊነት” በሚል መሪ ሀሳብ አሜሪካን አካዳሚ ኦፍ አቺቭመንት እና ግሎባል ሆፕ ኮአሊሽን የተሰኙት ተቋማት በዋሽንግተን ዲሲ በጋራ ባዘጋጁት ልዩ ዝግጅት ላይ፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የአረንጓዴ ዐሻራ ንቅናቄን አስመልክቶ ላሳዩት አመራር ‘የአፍሪካ የላቀ አመራር’ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።
ኢትዮጵያ በ2011 ዓ.ም. የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብርን ስታስጀምር፣ በአራት ዓመታት ውስጥ 20 ቢልዮን ችግኞችን ለመትከል ማቀዷ የሚታወስ ነው። ኢትዮጵያ ከታቀደው ግብ አልፋ በመላ ሀገሪቱ 25 ቢልዮን ችግኞች በመትከል የአራት ዓመት ዕቅዷን አሳክታለች። በዚህም የአየር ንብረት ለውጥን ለመቅረፍ እና ለደን መልሶ ልማት ላደረገችው አስተዋጽዖ በዓለም አቀፍ ደረጃ ዕውቅና አግኝታለች ሲል የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ዘግቧል።
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!
TikTok፡- tiktok.com/@aaeducationbureau
You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ…
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication
Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/
Website: – aaceb.gov.et
Email;- aacaebc@gmail.com
Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/