በአዲስ አበባ ከተማ ባሉ ክፍለ ከተሞች በዛሬው ዕለት ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ከተወጣጡ ነዋሪዎች ጋር በወቅታዊ ከተማዊ ጉዳይ ላይ ውይይት ተካሄደ።
ትኩረቱን የትምህርት ቤቶችን ሰላማዊ መማር ማስተማር ዙሪያ ያደረገው የውይይት መድረክ የትምህርት ተቋማትን መጠበቅና የተጣለባቸውን ተልእኮ እንዲወጡ ለማድረግ ህብረተሰቡ ኃላፊነቱን መወጣት እንዳለበት የተገለጸ ሲሆን ትምህርት ቤቶች በትምህርት ላይ ብቻ እንዲያተኩሩ ማድረግ እንደሚገባና ተቋማቱንና ተማሪዎችን ለሌላ ተልዕኮ መጠቀሚያ የሚያደርጉ አካላትንም መከላከልና አሥፈላጊውን እርምጃ መውሰድ እንደሚገባ ተነሥቷል።
በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ በውይይት መድረኩ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ የህዝብ ግንኙነት አማካሪ አቶ አለማየሁ እጅጉ፤ ሌላ የፖለቲካ አጀንዳ ያላቸው አካላት ሀገራዊ የልማትና ሠላም መሥፈንን ለማደናቀፍ በተለይም ትምህርት ቤቶቹን መጠቀሚያ ለማድረግ መሞከራቸውን ገልጸዋል።
ይሁን እንጂ የከተማ አሥተዳደሩ ከነዋሪው ጋር በመሆን ችግር በሚፈጥሩ አካላት ላይ አስፈላጊውን እርምጃ እንደሚወስድና የሚወድም ንብረትም የህዝብ በመሆኑ ማህበረሠቡ መጠበቅ እንደሚገባው አቶ አለማየሁ አሳስበዋል።
የውይይቱ ተሣታፊዎችም ወላጆች ልጆቻቸውን ከመቆጣጠር ጀምሮ ተቋማቱን በመጠበቅና ችግር የሚፈጥሩ አካላትን በማጋለጥ ከመንግሥት ጋር በትብብር መሥራት እንደሚገባ መጠቆማቸውን ሜር ኦፊስ ዘግባል።
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!
TikTok፡- tiktok.com/@aaeducationbureau
You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ…
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication
Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/
Website: – aaceb.gov.et
Email;- aacaebc@gmail.com