ቀን 29/3/2015 ዓ.ም

ፖሊስ በመዲናዋ በትምህርት ቤቶች ረብሻ ላይ ቀጥተኛ ተሳትፎ የነበራቸውን 97 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር ማዋሉን አስታወቀ፡፡

በመዲናዋ አዲስ አበባ በተለያዩ አካባቢዎች በሚገኙ ትምህርት ቤቶች ላይ ረብሻ ለማስነሳት የሞከሩና ቀጥተኛ ተሳትፎ የነበራቸውን 97 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር ማዋሉን የአዲስአበባ ፖሊስ አስታወቀ።

ፖሊስ “በቅርቡ በአዲስ አበባ በሚገኙ የተለያዩ ትምህርት ቤቶች በአንድ በኩል የዜጎችን በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው የመማር መብትና ማንነታቸውንና ባህላቸውን መግለፅን እንደ ጫናና በሃይል በሌሎች ላይ እንደተጫነ አድርጎ የመቀስቀስ በሌላ በኩል ደግሞ፤ የኦሮሞ ህዝብ እየሞተ ነው የህዝብ ባህልና ማንነት ተዋረደ የሚሉ እርስ በእርሱ የሚቃረን የግጭት ማቀጣጠያ  አጀንዳ በመፍጠር እንዲሁም፤ የወልቃይትና የአዲስ አበባ ጉዳይ አንድ ነው የሚል መፈክር ይዘው ከመውጣት ባሻገር  የሐገሪቱን ሰንደቅ ዓላማና የኦሮሚያ ክልል ባንዲራና ከሰንደቁ ላይ በማውረድና መሬት ለመሬት በመጎተት ከፍተኛ ድፍረት የፈፀሙ ግለሰቦች በቁጥጥር ሥር ውለዋል።” ብሏል፡፡

ሰሞኑን በተወሰኑ አንደኛና ጥቂት ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የጥፋት አጀንዳቸውን ከተቀበሉ አንዳንድ መምህራንና ተማሪዎች ጋር በመሆን በማደናገርና በማወናበድ ምንም የማያውቁ አብዛኛው ተማሪዎችን ከፊት በማሰለፍ ባስነሱት ረብሻ  በትምህርት ቤቶቹ ንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት እንዲደርስ ማድረጋቸውን መረጋገጡንም የአዲስአበባ ፖሊስ ገልጿል፡፡

ከዚህም በሻገር ፅንፈኛ በሆኑ ማህበራዊ ሚዲያዎቻቸው በመጠቀም የፀጥታ ሐይሉ ህጋዊ ተግባሩን እንዳይወጣ ለማሸማቀቅ ታስቦ ከዚህ በፊት የተቀረፁ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ምስሎችን እና እርምጃ ተወስዶ የታረመን ድርጊት አሁን እንደተፈፀመ በማስመሰልና በማሰራጨት ህብረተሰቡ ለአመፅና ብጥብጥ እንዲተባበር እያነሳሱ መሆናቸውን ፖሊስ በመረጃ ማረጋገጡን የገለጸ ሲሆን፤ ቀጥተኛ ተሳትፎ የነበራቸውን ዘጠና ሰባት ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ሥር አውሎ ምርመራ እያጣራ እንደሚገኝ ገልጿል፡፡

አያይዞም የፀጥታ ሐይሉ ከመቼውም ጊዜ በበለጠ በሐሠተኛ ሚዲያዎችና የሃሰት ዘገባዎች ሳይሸማቀቅ ከህዝብና ከመንግስት የተሰጠውን አደራ ለመወጣት ዝግጁ መሆኑን እና ህግ የማስከበር ግዴታውን እንደሚወጣ አስታውቋል፡፡

አዲስ አበባ የወትሮ ሠላሟና  የነዋሪዎቿ በሰላም ወጥቶ መግባት የሚያንገበግባቸው ግለሰቦችንና ሰላማዊ መማር ማስተማር ሂደቱን ለርካሽ የፖለቲካ አላማቸው ለማዋል እየተንቀሳቀሱ የሚገኙ ሃይሎችን ፤ በመለየት ህግ የማስከበር ተግባሩን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ያስታወቀው ፖሊስ፤ ህብረተሰቡም ልጆቹን ከመምከር ባሻገር የሠላሙ ፀር የሆኑ ግለሰቦችንና ቡድኖችን አጋልጦ ለፀጥታ አካላት በመስጠት የዘወትር ትብብሩን አጠናክሮ እንዲቀጥል  ጥሪውን አስተላልፏል፡፡ 

የፖሊስን አገልግሎት ለማግኘትና መረጃዎችን ለመስጠት በአዲስ አበባ ፖሊስ የመረጃ ስልክ ቁጥሮች 011-1-11-01-11 እና በነፃ የስልክ መስመር 991 ላይ በመደወል መረጃ መስጠት እንደሚቻል የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

ምንጭ፡- Mayor Office of Addis Ababa

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ

Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc

Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/

Website: – aaceb.gov.et

Email;- aacaebc@gmail.com

Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s