ቀን 26/3/2015 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ከቀዳማይ ልጅነት እድገትና እንክብካቤ ፕሮጀክት ጋር በመተባበር ለቅድመ አንደኛ ደረጃ መምህራን ለሶስተኛ ዙር የአቅም ግንባታ ስልጠና ሰጠ።

ስልጠናው በአማርኛና አፋን ኦሮሞ ስርዓተ ትምህርት ለሚያስተምሩ የቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መምህራን የተሰጠ ሲሆን ስልጠናውም ቀደም ሲል የአሰልጣኞች ስልጠና በወሰዱ 60 የቅድመ አንደኛ ደረጃ መምህራን ነው የተሰጠው፡፡

ስልጠናው በዋናነት መምህራኑ ህጻናቱን እያጫወቱ ማስተማር የሚችሉበትን ስነ-ዘዴ መሰረት በማድረግ ፤ የትምህርት እቅድ አዘገጃጀትን እንዲሁም የትምህርት መርጃ መሳሪያ ዝግጅትና የክፍል ውስጥ አደረጃጀትን መሰረት አድርጎ መሰጠቱን  በትምህርት ቢሮ የፕሮጀክቱ አስተባባሪ ወይዘሪት ትግስት ድንቁ ገልጸዋል፡፡

አስተባባሪዋ አክለውም በሶስተኛው ዙር ስልጠና በቅርቡ ወደ ማስተማር ስራው ለገቡ አዳዲስ የቅድመ አንደኛ ደረጃ መምህራን ቅድሚያ መሰጠቱን ጠቁመው እስካሁን በሶስቱ ዙሮች 4102 መምህራን ስልጠናውን መውሰዳቸውን በመጥቀስ በቀጣይ የአቅም ግንባታ ስልጠናውን ላልወሰዱ መምህራን ተመሳሳይ ስልጠና እንደሚሰጥ አስታውቀዋል፡፡

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ

Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc

Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/

Website: – aaceb.gov.et

Email;- aacaebc@gmail.com

Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s