ቀን 23/3/2015 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ አመራሮች እና ሰራተኞች የአረጋዊያንን ቤት ማደስ ጀመሩ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ አመራሮች እና ሰራተኞች ሙሉ ወጪ በመሽፈን በጉለሌ ክፍለ ከተማ በወረዳ 2 አስተዳደር ስር ለሚገኙ ሶስት ጣሪና ደጋፊ ለሌላቸው አረጋውያን በዛሬው እለት ቤት እድሳት እንዲጀመር አድርገዋል፡፡

በእድሳት ማስጀመሪያ መርሃ-ግብሩ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ ፣ የጉለሌ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ ወ/ሮ ቆንጂት ደበላ ፣ የወረዳ 2 ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ዩሐንስ ነጋሽ፣ የትምህርት ቢሮ ዳይሬክቶሬቶች እና ሰራተኞች ፣ እድሳቱ የሚደረግላቸው አረጋውያን ፣ በጎ ፍቃደኞች እና የአካባቢዉ ነዋሪዎች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ ባስተላለፉት መልዕክት የቤት እድሳቱ ሙሉ ወጪውን የሸፈኑት  የቢሮ ሰራተኞች በፈቃዳቸው መዋጮ አድርገው እንደሆነና  ቤቶቹ ተሰርተው ሲያልቁ የቢሮው አመራሮች ለአረጋውያኑ ሙሉ የቤት እቃ እንዲማላ እንደሚያደርጉላቸው ተናግረዋል፡፡ ሀላፊው አክለውም እድሳቱ በአጭር ጊዜ ውስጥ ተጠናቆ የትምህርት ቢሮ አመራሮች እና ሰራተኞች መጪውን የገናን በዓል በሚታደሱት ቤቶች ውስጥ ከአራጋዊያን ጋር በጋራ እንደሚያከብሩ ቃል ገብተዋል፡፡

የጉለሌ ክፍለከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ ወይዘሮ የሺ ደበላ በ2015 ዓ.ም በዘጠና ቀን ለ150 አነስተኛ ገቢ ላላቸው ነዋሪዎች የቤት እድሳት ለማድረግ እቅድ መያዙንና ስራው የተጀመረ መሆኑን ገልጸው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ላደረገው ቀና ትብብር ምስጋና አቅርበዋል፡፡

የጉለሌ ክፍለከተማ ወረዳ ሁለት ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ዩሐንስ ነጋሽ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደሩ ትምህርት ቢሮ  በወረዳ 2 ስር እንደሚገኝ በመጥቀስ የወረዳ አስተዳደሩ የለበትን የኮንፒተር እና የተለያዩ የቢሮ ግብዓቶች ችግር ለቢሮ በማቅረባቸው ቢሮ ችግሩን በሙሉ እንደቀረፈላቸው በመጥቀስ ለአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ ሚስጋና አቅርበዋል፡፡

የቤት እድሳት የተደረገላቸው ነዋሪዎች እንደገለጹት ቤቱ ለመኖር አመቺ እንዳልሆነና ዝናብ በሚመጣ ስአት በሰቀቀቀን እንደሚኖሩና ቤታቸውን ለማደስ ቀርቶ የእለት ምግብ ለማግኘት እንደሚቸገሩ ተናገረው ስለተደረገላቸው የቤት እድሳት በጣም ደስተኛ መሆናቸውን በመግለጽ ለትምህርት ቢሮ ምስጋና አቀርበዋል፡፡

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ

Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc

Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/

Website: – aaceb.gov.et

Email;- aacaebc@gmail.com

Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s