አለም አቀፍ የኤች አይ ቪ ኤድስ ቀንን በማስመልከት የፓናል ውይይት ተደረገ፡፡
የፓናል ውይይቱን ያደረጉት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሰራተኞች ሲሆኑ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የኤች አይ ቪ ኤድስ መከላከልና መቆጣጠር ባለሙያ ወይዘሪት ገንዘብ ደሳለኝ ዘንድሮ ቀኑ በአለም አቀፍ ደረጃ ለ35ኛ እንዲሁም በሀገራችን ለ34ኛ ጊዜ ፍትሀዊና ተደራሽ የኤች አይ ቪ ኤድስ አገልግሎት በሚል መሪ ቃል የተከበረ መሆኑን ጠቁመው ፍትሀዊና ተደራሽ የኤች አይ ቪ ኤድስ አገልግሎት የሚለው መሪ ቃል ኤች አይ ቪ ኤድስ በደማቸው ያለባቸውን ወገኖቻችንን በቂ የህክምና ክትትል እንዲያደርጉ ማመቻቸትን ፣ መገለልና አድሎን ማስቀረትን ፣ ልዩትኩረትና እገዛ ማድረግን እንዲሁም ፍትሃዊ የሆነ አገልግሎት መስጠትን የሚጠቁም መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡
ወይዘሪት ገንዘብ አክለውም ከ1981 ጀምሮ በአለም አቀፍ ደርጃ ከ32.7 ሚሊዮን በላይ ሰዎች ህይወታቸውን በኤድስ ምክንያት ያጡ ሲሆን 38 ሚሊየን ሰዎች ደግሞ በአሁኑ ጊዜ ኤች አይ ቪ በደማቸው እንደሚኖር ይገመታል ብለዋል፡፡ በየአመቱ 1.7 ሚሊየን የሚሆኑ አዲስ በኤች አይ ቪ የሚያዙ ሰዎች እንዳሉና 690,000 ሰዎች ለህልፈተ ህይወት እንደሚዳረጉ መረጃዎች ያሳያሉ ብለዋል፡፡ አክለውም 44.1 ሴቶች፤51.5 ወንዶች ብቻ መሰረታዊ የኤች አይ ቪ ኤድስን የመከላከል እውቀቱ ያላቸው መሆኑን ተናግረዋል፡፡
የውይይቱ ተሳታፊ የሆኑት ሰራተኞች በበኩላቸው እለቱን አከብሮ መዋል እራስንና ቤተሰብን ለመጠበቅ ጥሩ ማስታወሻ መሆኑን ጠቁመው በትምህርት ቤት ያሉ ክበባትም ኤች አይ ቪ ኤድስ የበለጠ ትኩረት ተደርጎ ቢሰራበት እንዲሁም በትምህርት ቤቶች ያሉ የስነ-ልቦና ባልሙያዎችን ለተማሪዎች ግንዛቤ የመፍጠር ስራ ቢያከናውኑ ስርጭቱን የተሻለ መቀነስ የሚቻል መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!
You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ…
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication
Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/
Website: – aaceb.gov.et
Email;- aacaebc@gmail.com
Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/