ቀን 22/3/2015 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ከአዲስ አበባ ጤና ቢሮ ጋር በመተባበር አለም አቀፉን የኤች አይ ቪ ኤድስ ቀን በቀጨኔ ደብረ ሰላም 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አከበረ ።

እለቱ ዘንድሮ በአለም አቀፍ ደረጃ ለ35ኛ እንዲሁም በሀገራችን ለ34ኛ ጊዜ ፍትሀዊና ተደራሽ የኤች አይ ቪ ኤድስ አገልግሎት በሚል መሪ ቃል የሚከበር ሲሆን በመርሀ ግብሩ በትምህርት ቤቱ ተማሪዎች ቀኑን የተመለከቱ የተለያዩ የኪነጥበብ ስራዎች ቀርበዋል ።

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ የኤች አይቪ ኤድስ ዘርፈ ብዙ ምላሽ ቡድን መሪ ሲስተር ሂሩት አለማየሁ በመርሀ ግብሩ ባስተላለፉት መልዕክት ቫይረሱ ከ1981ዓ.ም ጀምሮ በሰው ልጆች ላይ የተለያዩ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ማስከተሉንና በርካቶችን ለሞት ሲዳርግ መቆየቱን ገልጸው በአዲስ አበባ የቫይረሱ ስርጭት አሁንም ቢሆን ከፍተኛ ከመሆኑ ባሻገር  ታዳጊ ወጣቶች ለቫይረሱ ተጋላጭ በመሆናቸው ሀገራችን እ.አ.አ በ2030 ከኤች አይ ቪ ኤድስ ነፃ የሆነ ትውልድ ለመፍጠር የያዘችው እቅድ እንዲሳካ የትምህርት ሴክተሩ ድርሻ የላቀ መሆኑን አስረድተዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የኤች አይ ቪ ኤድስ መከላከልና መቆጣጠር ባለሙያ ወይዘሪት ገንዘብ ደሳለኝ በበኩላቸው በትምህርት ሴክተሩ የቫይረሱን ስርጭት ለመቆጣጠርም ሆነ ለመከላከል ክበባትን ከማደራጀትና ድጋፍ ከማድረግ ጀምሮ የተለያዩ ግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኮች ሲዘጋጁ መቆየታቸውን ጠቁመው ወረርሽኙ በዋናነት በአፍላ እድሜ ላይ የሚገኙ ወጣቶችን እያጠቃ በመገኘቱ ተማሪዎች እራሳቸውንና አከባቢያቸውን ከቫይረሱ መከላከል እንደሚገባቸው አስገንዝበዋል።

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ

Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc

Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/

Website: – aaceb.gov.et

Email;- aacaebc@gmail.com

Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s