የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ አለም አቀፉን የጸረ ሙስና ቀን በማስመልከት ሙስናን መታገል በተግባር በሚል መሪ ቃል የተለያዩ የትምህርት ባለድርሻ አካላት በተገኙበት የፓናል ውይይት አካሄደ።
በውይይቱ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የስነምግባርና ጸረ ሙስና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ አስራት ሽፈራው ከፌደራል ስነምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን የወረደን ሰነድ ከተቋሙ ነባራዊ ሁኔታ ጋር በማስተሳሰር ያቀረቡ ሲሆን የትምህርት ሴክተሩ ሙስናንም ሆነ ብልሹ አሰራርን ለመታገል በየትምህርት ቤቶቹ የተደራጁ የስነ ምግባርና ጸረ ሙስና ክበባትን ከማጠናከር ጀምሮ ለተማሪዎች የግብረ ገብነትን ትምህርት በአግባቡ ማስተማር እንደሚገባ አስረድተዋል ።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ዳኘው ገብሩ በውይይቱ ባስተላለፉት መልዕክት መንግስት ሙስና የሚያስከትለውን ችግር ለመከላከል በሰጠው ከፍተ ኛ ትኩረት ብሔራዊ የፀረ ሙስና ኮሚቴ ከማቋቋም ጀምሮ የተለያዩ ጥረቶችን በማድረግ ላይ እንደሚገኝ ገልጸው የትምህርት ማህበረሰቡም ሙስናንም ሆነ ብልሹ አሰራርን ለመከላከል በሚደረገው እንቅስቃሴ ከችግሩ ጋር በተገናኘ የሚስተዋሉ የአስተሳሰብ ዝንፈቶችን በማስተካከል ሙስናን የሚጸየፍ ትውልድ ማፍራት እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊው አቶ ሳምሶን መለሰ በበኩላቸው ከሀገራዊ ለውጡ ከሙስናም ሆነ ብልሹ አሰራር በተገናኘ ለሚካሄደው ትግል ምቹ ሁኔታን መፍጠሩን ጠቁመው ችግሩን ለመከላከል ተቋማዊ አሰራርና አደረጃጀትን በማጠናከር ደንብና መመሪያን ተከትሎ መስራት እንደሚገባ አስታውቀዋል።
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!
You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ…
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication
Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/
Website: – aaceb.gov.et
Email;- aacaebc@gmail.com
Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/