ቀን 19/3/2015 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ዘንድሮ ለ17ኛ ጊዜ ህብረ ብሔራዊ አንድነታችን ለዘላቂ ሰላማችን በሚል መሪ ቃል የሚከበረውን የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ቀንን በማስመልከት ከትምህርት ቤት ጀምሮ በየደረጃው ሲያካሂድ የነበረውን የፓናል ውይይት በዛሬው እለት አጠናቀቀ፡፡

ውይይቱ ዛሬ በቢሮ ደረጃ ሲጠቃለል በየደረጃው የሚገኙ የትምህርት አመራሮችና ባለሙያዎችን ጨምሮ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መምህራን ማህበር አመራሮችእና የወላጅ ማህበር ተወካዮች መምህራን እንዲሁም ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው አካላት በተገኙበት የተካሄደ ሲሆን በመርሀ ግብሩ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የስነ ዜጋና ስነምግባር ስርአተ ትምህርት ባለሙያው አቶ ዘሪሁን አለማየሁ በፌደራሊዝም ስርአት ጽንሰ ሀሳብ ምንነትና ተዛማጅ ርዕሰ ጉዳይ ዙሪያ  ጽሁፍ አቅርበው ውይይት ተካሂዱዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ በመርሀ ግብሩ ባስተላለፉት መልዕክት ዘንድሮ ለ17ኛ ጊዜ ህብረ ብሔራዊ አንድነታችን ለዘላቂ ሰላማችን በሚል መሪ ቃል የሚከበረውን የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ቀንን በማስመልከት ተመሳሳይ ውይይት ከትምህርት ቤት ጀምሮ በየደረጃው ባሉ መዋቅሮች ሲካሄድ መቆየቱን ገልጸው በውይይቶቹም በዋናነት በሀገራዊም ሆነ ህገመንግስታዊ ጉዳዮች የጋራ አስተሳሰብ በመያዝ ዘላቂ ሰላምን ለማረጋገጥ የሚያስችሉ ሀሳቦች መነሳታቸውን አስረድተዋል፡፡

ዶክተር ዘላለም አክለውም ኢትዮጵያ ከወሰነቻቸውና በታሪክ ከሚነሱ ውሳኔዎች መካከል አንዱ የፌደራል ስርአቱን ተግባራዊ ያደረገችበት አጋጣሚ መሆኑን ጠቁመው የትምህርት ማህበረሰቡ በህገመንግስቱም ሆነ የፌደራል ስርአቱ ዙሪያ ተገቢውን ግንዛቤ ጨብጦ የትምህርት ልማት ስራውን ውጤታማ ማድረግ እንደሚጠበቅበት አስገንዝበዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ዳኛው ገብሩ የፌደራል ስርአቱ የህዝቦችን እኩልነትና እራስን በራስ የማስተዳደር መብት ያከበረ በመሆኑ ከጽንሰ ሀሳቡ ጋር በተገናነ የሚታዩ የተዛቡ አስተሳሰቦችን በማረም ብዝሀነትን ያከበረ ስርአት መፍጠር እንደሚገባ ሲገልጹ የቢሮው ምክትል ኃላፊ አቶ አድማሱ ደቻሳ በበኩላቸው የጋራ የሆነችውን ሀገራችንን በሚፈለገው ደረጃ ለመገንባት ህብረብሄራዊ አንድነታችንን አጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባ አስታውቀዋል፡፡

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ

Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc

Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/

Website: – aaceb.gov.et

Email;- aacaebc@gmail.com

Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s