ቀን 14/3/2015 ዓ.ም

የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት 17ኛውን የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ቀንን ምክንያት በማድረግ የባህል ሲምፖዚየም አካሄደ፡፡

‹‹ህብረ ብሄራዊ አንድነታችን ለዘላቂ ሰላማችን›› በሚል መሪ ቃል የ2015 ዓ.ም 17ኛውን የብሔር ብሔረሰቦች ቀንን ስናከብር ያሉን ባህላዊ እሴቶች አንድነታችንን የሚያጠናክሩና የኢትዮጵያዊነታችን መገለጫ ስለሆኑ ልንጠብቃቸውና ለሌሎች ልናጋራቸው ይገባል ሲሉ የክፍለ ከተማው ትምህርተ ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሪት ሳምራዊት ቅባቱ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር ገልፀዋል፡፡

በፊሊጶስ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት በተካሄደው የባህል ሲንፖዚየም በ1ኛና 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች የተዘጋጁ የብሄር ብሄረሰብ አልባሳት፣ ባህላዊ ምግቦች፣ ባህላዊ ውዝዋዜዎች እና ባህላዊ መጠቀሚያ እቃዎች በማሳየት በተደረገው የባህል ሲምፖዚየም ላይ ውድድር በማካሄድ ስራቸውን ላቀረቡ ት/ቤቶች በሙሉ የተሳትፎ የምስክር ወረቀት እንዲሁም ከ1ኛ እስከ 3ኛ ለወጡ ት/ቤቶች የዋንጫ እና የምስክር ወረቀት በመስጠት በደማቅ ሁኔታ መካሄዱን ከክፍለ ከተማው ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያሳያል፡፡

ደረጃ ይዘው ያጠናቀቁ ት/ቤቶች የሚከተሉት ናቸው፡-  

  1. ፊሊጶስ ቅድመ አንደኛ እና የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት፡- 93.9 ውጤት በማስመዝገብ 1ኛ ደረጃ
  • አበቦች ፍሬ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት፡-  93.1ውጤት በማስመዝገብ 2ኛ ደረጃ
  • ጉለሌ ፋና የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት፡- 88.1 ውጤት በማስመዝገብ 3ኛ ደረጃ ተብለው የዋንጫ ተሸላሚ ሆነዋል፡፡

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ

Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc

Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/

Website: – aaceb.gov.et

Email;- aacaebc@gmail.com

Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s