ቀን 14/3/2015 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ዘንድሮ ለ17ኛ ጊዜ “ህብረ ብሔራዊ አንድነታችን ለዘላቂ ሰላማችን!” በሚል መሪ ቃል የሚከበረውን የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ቀንን በማስመልከት በተማሪዎች መካከል የጥያቄና መልስ ውድድር አካሄደ፡፡

የጥያቄና መልስ ውድድሩ ቀደም ብሎ ከትምህርት ቤት ጀምሮ እስከ ክፍለከተማ ድረስ ተካሂዶ አሸናፊ ሆነው በቀረቡ ተማሪዎች መካከል የተካሄደ ሲሆን በውድድሩም ከአስራ አንዱ ክፍለ ከተሞች በአማርኛና አፋን ኦሮሞ ስርዓተ ትምህርት የሚማሩ 22 የ7ኛ እና 8ኛ ክፍል ተማሪዎች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የስርዓተ ትምህርት ዝግጅትና ትግበራ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተሩ አቶ ጌታቸው ታለማ በጥያቄና መልስ ውድድሩ ማስጀመሪያ መርሀ ግብሩ ባስተላለፉት መልዕክት በተማሪዎች መካከል የሚካሄደው የጥያቄና መልስ ውድድሩ ዘንድሮ ለ17ኛ ጊዜ የሚከበረውን የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ቀንን በማስመልከት ህገ መንግስቱን እና ፌደራሊዝም ስርአቱን መሰረት ባደረጉ ጥያቄዎች እንደሚካሄድ ገልጸው በዛሬው ውድድር አሸናፊ የሆኑ ተማሪዎችም በመጪው ቅዳሜ በድምቀት በሚካሄደው የአሸናፊዎች አሸናፊ ወድድር ላይ ተሳታፊ እንደሚሆኑ አስታውቀዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የአፋን ኦሮሞ ስርዓተ ትምህርት ዝግጅት ትግበራና አጠቃላይ ሱፐር ቪዥን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሮቢ ዋሚ በበኩላቸው በተማሪዎች መካከል የሚካሄደው የጥያቄና መልስ ውድድር ዘንድሮ ለ17ኛ ጊዜ ህብረ ብሔራዊ አንድነታችን ለዘላቂ ሰላማችን በሚል መሪ ቃል የሚከበረውን የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ቀንን በማስመልከት የሚካሄድ መሆኑን ጠቁመው ውድድሩ ተማሪዎቻችን በትምህርት ስርአቱ ህገመንግስቱንም ሆነ የፌደራል ስርአቱን መሰረት በማድረግ የሚሰጠውን ትምህርት በአግባቡ መረዳታቸውን ለማረጋገጥ እንደሚረዳ  ገልጸዋል፡፡

በጥያቄና መልስ ውድድሩ በአማርኛው ስርዓተ ትምህርት አራዳ፤ልደታ፤አዲስ ከተማ፤ኮልፌ ቀራንዮ እና አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተሞች አሸናፊ ሆነው ለፍጻሜ ማለፋቸውን በአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ የስነ-ዜጋና ስነ-ምግባር ስርዓተ ትምህርት ዝግጅት ባለሙያው አቶ ዘሪሁን አለማየሁ ሲገልጹ በአፋን ኦሮሞ ስርዓተ ትምህርት ደግሞ አራዳ፤ኮልፌቀራንዮ፤አቃቂ ቃሊቲ፤ ንፋስ ስልክ ላፍቶ እና ቦሌ ክፍለከተሞች አሸናፊ በመሆን በመጪው ቅዳሜ ለሚካሄደው የአሸናፊዎች አሸናፊ ውድድር ማለፋቸውን ገልጸዋል፡፡ 

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ

Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc

Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/

Website: – aaceb.gov.et

Email;- aacaebc@gmail.com

Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s