ቀን 9/3/2015 ዓ.ም

በልደታ ክ/ከተማ ት/ጽ/ቤት 17ኛውን የብሔር ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ቀን በዓልን “ህብረ ብሔራዊ አንድነታችን ለዘላቂ ሰላም “በሚል መሪ ቃል በተለያዩ መርሃ ግብሮች አከበረ።

በበዓሉ ላይ የክፍለ ከተማው ት/ጽ/ቤት ሀላፊ ወ/ሪት እጅጋየሁ አድማሱ በመገኘት ጥሪ የተደረገላቸውን እንግዶች እንኳን ደህና መጣችሁ በማለት 17ተኛው የብሔር ብሔረሰቦችን ቀንን ስናከብር ከሌላው ጊዜ በተለየ ሁኔታ የምናከብር ሲሆን በዝግጅቱ ላይም ፌስቲቫል የተለያዩ ትዕይንቶችና እንዲሁም የፓናል ውይይት የተማሪዎች ህገ መንግስትን መሠረት ያደረገ ጥያቄ እና መልስ ውድድር የተደረጉ ሲሆን ይህም እስከ ህዳር 29 ይቀጥላል ብለዋል።

ብሔር ብሔረሰብ ቀንን ስናከብር አንድነታችንን እና እሴታችንን ሊያጠናክር የሚችል ሀገረ መንግስት የምናጎለበትበት ሲሆን ሀገራችን ከ80 በላይ ብሔር ብሔረሰቦች በወንድማማችነት እና በህትማማችነት የሚኖሩባት የነዚህን ባህል ቱፊት ማጠናከር መቻል በሚያስችል አግባብ መሆን አለበት በማለት ገልፀዋል።

በመቀጠልም የምክር ቤት ምክትል አፈ- ጉባዔ ወ/ሮ ሰርካለም አበበ ብሔር ብሔረሰብን ስናከብር በባለፈው ስርዓት የሚነሱ የባህል የቋንቋ የሀይማኖት ጥያቄዎችን ለመመለስ የሚያስችል የኢፌዲሪ ህገ መንግስት ህዳር 29/1987 የፀደቀ ሲሆን በ1998 ጀምሮ በአገራችን ለ17ተኛ ጊዜ እየተከበረ ይገኛል ሲሉ ገልፀዋል።

በት/ጽ/ቤት የስራዓተ ትምህርት ቡድን መሪ የሆኑ አቶ ገዳ ሞሲሳ የብሔር ብሔረሰብ ቀን በትምህርት ተቋም ስናከብር ትልቅ ቦታ በመስጠት በዓሉ የሚከበር ሲሆን ልዩነታችን ውበታችን መሆኑን አውቀን በደመቀ መልኩ እናከብራለን ብለዋል።

በመጨረሻም ለፓናል ውይይቱ የሚሆን ሰነድ ከመድረክ በዝርዝር ቀርቦ በቀረበው ሰነድ ላይ የተለያዩ አስተያየት ሀሳብ እና ጥያቄ የቀረበ ሲሆን በቀረቡት ላይ የትምህርት ጽ/ቤት ሀላፊ ወ/ሪት እጅጋየሁ እና የምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባዔ ወ/ሮ ሰርካለም አበበ ማጠቃለያ ሀሳብ መስጠታቸውን ከክፍለ ከተማው ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ

Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc

Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/

Website: – aaceb.gov.et

Email;- aacaebc@gmail.com

Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s