የፓናል ውይይት ለሚያወያዩ አስልጣኞች የአስልጣኞች ስልጠና ተሰጠ፡፡
በአስልጣኞች ስልጠና መድረክ ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ አማካሪ የሆኑት ወ/ሮ አበበች ነጋሽ በሀገራችን ‘’ህብረብሄራዊ አንድነታችን ለዘላቂ ሰላማችን!’’ በሚል መሪ ቃል ዘንድሮ ለ17ኛ ጊዜ የሚከበረው የኢትዮጵያ ብሄሮች ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ቀን በአዲስ አበባ በሁሉም የትምርት መዋቅር መለትም በቢሮ ፣ በክፍለ ከተማ ፣ በወረዳ እና በትምህርት ቤት ደረጃ በተማሪዎች የጥያቄና መልስ ውድድሮች ፣ በፓናል ውይይቶች እና ህብረብሄራዊነትን በሚያሳዩ ትዕይንቶች የሚከበር መሆኑ ጠቅሰዋል፡፡
ሀላፊዋ አክለውም የአስልጣኞች ስልጠና መስጠት ያስፈለገበትን ምክንያት ሲገልጹ በየደረጃው የሚደረገው የፓናል ውይይት በሀገር አቀፍ ደረጃ የተዘጋጀ በመሆኑ ዛሬ በስልጠናው ላይ የተሳተፉ አካላት መጨበጥ የሚገባቸውን ዋና ዋና ነጥቦች እንዲይዙ እና በቀጣይ በየደረጃው ለሚደረጉ የፓናል ውይይት አወያዮች ተመሳሳይ ግንዛቤ እንዲጨብጡ ለማድረግ ታስቦ የተካሄደ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ አማካሪ አቶ ጥላሁን ፍቃዱ በበኩላቸው በሀገራችን ሰላም እንዲረጋገጥ በጋራ ተግባብቶና ተናቦ መስራ እንደሚያስፈልግ ገልጸው ህብረብሄራዊነታችን ለአንድነታችን መረጋገጫ እና ለሰላማችን መበልጸግ የሚኖረው ሚና የጎላ በመሆኑ ስልጣኞች የሚሰጣቸውን ስልጠና በመውሰድ የታለመው ግብ እዲሳካ መስራት ይገባል ብለዋል፡፡
በአስልጣኞች ስልጠና መድረኩ ስልጠናው በአቶ ዘሪሁን አለማየሁ የተሰጠ ሲሆን ከ11ዱም ክፍለ ከተማዎች የተውጣጡ ባለሙያች እና መምህራን ተሳታፊ ሆነዋል፡፡
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!
You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ…
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication
Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/
Website: – aaceb.gov.et
Email;- aacaebc@gmail.com
Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/