“ህብረ ብሔራዊ አንድነታችን ለዘላቂ ሰላማችን” በሚል መሪ ቃል ለ17ኛ ጊዜ የሚከበረውን የ2015 ዓ.ም የኢትዮጵያ ብሄሮች ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ቀንን በማስመልከት በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ የተማሪዎች ጥያቄና መልስ ውድድር ተካሄደ፡፡
በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ውስጥ በሚገኙ 1ኛና 2ኛ ደረጃ የመንግስትና የግል ት/ቤት ተማሪዎች ለ17ኛ ጊዜ የሚከበረውን የኢትዮጵያ ብሄሮች ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ቀን በዓልን በየት/ቤቶች በተለያዩ ዝግጅቶች በደመቀ ሁኔታ እየተከበረ መሆኑና ከበዓሉ አከባበር አንዱ የሆነው በክፍለ ከተማው ትምህርት ጽ/ቤት አዘጋጅነት የተካሄደው የተማሪዎች የጥያቄና መልስ ውድድር ሲሆን ብርቱ ፉክክር የተደረገበት መሆኑን እና በቀጣይ ተማሪዎች በሀገርና በአለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ እንዲሆን ለማድረግ እንደሚያግዝ የክፍለ ከተማው ትምርት ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሪት ሳምራዊት ቅባቱ ገልጸዋል፡፡
ሃላፊዋ አክለውም በስነ-ምግባራቸው ተማሪዎች የተመሰገኑ፣ ውጤታማ እና ተወዳዳሪ እንዲሆኑ በፕሮግራሙ ላይ ለተገኙ ተማሪዎች መልእክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
በአቢሲኒያ ሁለተኛ ደረጃና በእድገት አንደኛ ደረጃ ት/ቤቶች በተካሄደው የጥያቄና መልስ ውድድር ለአሸናፊ ተማሪዎችና ት/ቤቶች የማበረታቻ ሽልማት መበርከቱን ከክፍለ ከተማው ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያሳያል፡፡
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!
You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ…
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication
Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/
Website: – aaceb.gov.et
Email;- aacaebc@gmail.com
Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/