ቀን 6/3/2015 ዓ.ም

በአንደኛ ደረጃ ትምህርት  ቤቶች እየተደረገ ያለው የትምህርት ቤት ምገባ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ አስገነዘቡ፡፡

በአንደኛ ደረጃ ትምህርት  ቤቶች እየተደረገ ያለው የትምህርት ቤት ምገባ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ገልጸዋል ።

በዚህ ዓመት ከ200ሺ በላይ ተጨማሪ ተማሪዎችን መመገብ  የሚያስችል አቅም መፈጠሩንም ጠቁመዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዛሬ ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች በሰጡት ማብራሪያ በትምህርት ቤት ምገባ መርሀ ግብር እየተከናወነ ያለው ስራ የሚያስደስትና ሊኮራበት የሚገባው ነው ብለዋል።

በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ  ዘጠን ነጥብ አምስት ሚሊዮን ተማሪዎች በቀን ሁለት ጊዜ  በትምህርት ቤት መመገብ መቻሉን  ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ  አብራርተዋል፡፡

በዚህም  ባለፈው ዓመት ከነበረው ዘጠኝ ነጥብ አራት ሚሊዮን ተማሪዎች  ቁጥር ጋር ሲነጻጸር  ከሁለት መቶ ሺህ በላይ ተማሪዎች መጨመር የሚያስችል አቅም መፈጠሩን አመላክተዋል፡፡

የሁሉ ነገር መሰረት በሆነው የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎችን መመገብ በምግብ እጦት ምክንያ ነገ ሳይንቲስቶች ፣ ሀኪሞችና ኢንጂነሮች ሊሆኑ የሚችሉ ተማሪዎች ትምህርት እንዳይስተጓጎል መርዳት መሆኑንም አስታውሰዋል፡፡

የትምህረት ቤት ምገባ መርሀ ግብሩ ከኑሮ ውድነቱ ጋር በተያያዘ ልጆቻቸውን ትምህረት ቤት መላክ ያልቻሉ ወላጆችን መደገፍ  ጭምር መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስገንዝበዋል፡፡

በመሆኑም በአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች እየተካሄደ ያለው የተማሪዎች ምገባ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባም ጠቅላይ ሚኒስትሩ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ማብራሪያው አሳስበዋል፡፡

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ

Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc

Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/

Website: – aaceb.gov.et

Email;- aacaebc@gmail.com

Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s